ታዋቂው የባንክ ባለሙያ፤ አቶ ተፈራ ደግፌ አጭር ታሪክ
Ethiopia Zare (እሁድ የካቲት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. March 08, 2015፦) የቀድሞ የኢትዮጵ ብሄራዊ ባንክ ገዢ የነበሩትና፤ በኢትዮጵያ ለባንክ ስራ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት፤ አቶ ተፈራ ደግፌ፤ ባለፈው አርብ ማርች 6 ቀን፤ 2015 ዓ.ም. ቫንኩቨር በሚገኝ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው፤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።