እቴጌ ጣይቱ ብጡል በዘመናዊት ኢትዮጵያ የአገር ግንባታ ሂደት የተጫወቱት ሚና- ሞረሽ ወገኔ ቅፅ 3 ፣ ቁጥር 2
ለዐድዋ ድል 119ኛ ዓመት መታሠቢያ በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተዘጋጀ
1. መግቢያ
ኢትዮጵያ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ዐድዋ ላይ በጣሊያን ቅኝ ገዥ ኃይል ላይ የተጎናጸፈችው ድል፣ የዓለምን አመለካከት እና በሰው ልጆች መካከል መኖር የሚገባው ግንኙነት ምን መሆን እንዳለበት ከመሠረቱ ቀይሮታል። ድሉ፣ አውሮፓውያን በጥቁር ሕዝብ ላይ የነበራቸውን የበላይነት ስሜት ደጋግመው እንዲያጤኑ እና ይህን ስሜታቸውን እንዲለውጡ ያስገደደ መሆኑ ግልፅ ነው። ከዚህ አልፎም የዐድዋ ድል በአውሮፓውያን ቅኝ ግዛት ሥር የነበሩ የአፍሪካ፣ የእስያ እና የላቲን አሜሪካ ዜጎች ለነፃነታቸው እንዲታገሉ የኅሊና ስንቅ፣ የመንፈስ ብርታት፣ እንዲሁም የማድረግ ቁርጠኝነትን አስጨብጧል ማለት ይቻላል። ይህም በመሆኑ ድሉ፣ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን፣ የመላው ጥቁር ሕዝብ፣ ከዚያም በላይ በቅኝ ግዛት ሥር የነበሩ የዓለም ሕዝብ ሁሉ ነው ተብሎ ይወደሣል። ይህ ድል የዘመኑ ኃያላን አገሮች ሳይወዱ በግድ፣ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት፣ ነፃነት፣ ሉዐላዊነት እና አገራዊነት አምነው በመቀበል አንፃራዊ በሆነ መልኩ በዕኩልነት ላይ የተመሠረተ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲመሠርቱ አስገድዷቸዋል። ከሁሉም በላይ የዐድዋ ድል በቅኝ ግዛት ቀንበር ተጠምደው ፍዳቸውን ያዩ የነበሩት አፍሪቃውያን፣ ለነፃነታቸው በቁርጠኝነት እንዲታገሉ የነፃነት ቀንዲል፣ የቁሣዊ እና ኅሊናዊ ስንቅ ምንጭ፣ የወኔ ቋት፣ የመሥዋዕትነት ክብር እና ዋጋ መስታወት ሆኖ አገልግሏል። በመሆኑም ድሉ የቅኝ ገዥዎችን ኃይል በማዳከም የቅኝ ተገዥዎችን ብርታት በማጎልበት፣ በፖለቲካ መስኩ አፍሪቃ በአፍሪቃውያን እንድትመራ ሠፊ በር የከፈተ መሆኑ ወዳጅም ጠላትም የተቀበሉት ሃቅ ነው። ስለሆነም የዘንድሮውን የዐድዋ ድል 119ኛ ዓመት አስበነው የምንውለው፣ ድሉ በፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግሉ ባስመዘገበው አኩሪ የነፃነት ስሜት፣ እንዲሁም ለቅኝ ተገዥ አገሮች ዜጎች ባስገኘው የማንነት ባለቤትነት ውጤት ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተዘከረ እንዲታሰብ ለማድረግ ነው።……… (ሙሉውን ከዚህ ላይ ያንብቡ….,
The post እቴጌ ጣይቱ ብጡል በዘመናዊት ኢትዮጵያ የአገር ግንባታ ሂደት የተጫወቱት ሚና- ሞረሽ ወገኔ ቅፅ 3 ፣ ቁጥር 2 appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.