ነዳጅ ከመሸጫ ዋጋ በላይ የሚሸጡ ነጋዴዎችን እስከ 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ አዋጅ ጸደቀ
በአዋጁ መሠረት “የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጪ የሚያከማቹ፣ እና ከግብይት ሥርዓት ውጪ ሲሸጡ የተገኙ” ሰዎች፤ ከሦስት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እሥራት እና ከ350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣሉ። ከቅጣቱ በተጨማሪ “ማንኛውም የነዳጅ ውጤቶች አጓጓዥ ተሸከርካሪ ጂፒኤስ የመግጠም ግዴታ አለበት” የሚል አዲስ ድንጋጌ ተካትቶበታል።