ኦሮምኛ ለፌደራል መንግስት – እንዴት?

(አዲስ ከድሬዳዋ) በሶሻል ሚዲያ(በተለይ በፌስቡክ) ብዙ ጊዜ አስተማሪና ምክንያታዊ የሆኑ ፅሑፎችን በመፃፍ የሚታወቀው ዶክተር ብርሀነ መስቀል አበበ ሰኚ ሰሞኑን ከአማርኛ ጎን ለጎን ኦሮምኛም የፌደራል መንግስት፣ እንዲሁም የድሬዳዋ እና የአዲስአበባ አስተዳደሮች የስራ ቋንቋ እንዲሆን የሚጠይቁ ፅሑፎችን በተከታታይ እያወጣ ሰፊ ውይይትም እየተደረገ ነው፡፡ ሀሳቡንም በግሌ እደግፈዋለሁ፡፡ነገር ግን በምን መልኩ ነው የስራ ቋንቋ የሚሆነው , እንዲሁም በአተገባበር ሒደት ምን ሊያጋጥም ይችላል የሚለው ግን የታሰበበት አይመስልም፡፡ ኦሮምኛን የስራቋንቋ ይሁን ስንል የሀገሪቱ የቋንቋ አጠቃቀም ፖሊሲ ምን ይመስላል የሚለውን በጨረፍታ ማየት የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የላትም፡፡ በሀገሪቱ የሚነገሩ ቋንቋዎች ሁሉም እኩል ናቸው፡፡ በርካታ ወይም አነስተኛ ተናጋሪ ስላለው አንድ ህዝብ በአፍ መፍቻ ቋንቋው እንዳይማር፣ አገልግሎት እንዳገኝ፣ እንዳይዳኝ፣ . . . . አይከለከልም፡፡ሆኖም ከኢኮኖሚ አቅም እና የተማረ የሰው ሀይል ውስንነት ጋር ተያዞ በመማሪያነት እያገለገሉ ያሉ ቋንቋዎች ከ30 አይበልጡም(በርግጥ ይህ ከ90 ፐርሰንት በላይ ኢትዮጵያውያንን ይሸፍናል)፡ ስለዚህ ሁሉም ቋንቋ እኩል ከሆኑ አንድን ቋንቋ የፌደራል የስራ ቋንቋ አድርገህ ሁሉም ክልሎች በትምህርት ቤቶቻቸው እንዲስተምሩት፣ በጋራ መግባቢያነት እንዲጠቀሙት፣ . . ለመወሰን የተለየ መነሻ ያስፈልጋል፡፡በዚህ ረገድ አማርኛ በ ታሪክ አጋጣሚ በብዙ ቦታዎች በሁለተኛ ቋንቋነት፣ በጋራ መግባቢያነት ( lingua franca) ና በመንግስት ቋንቋነት ሲያገለግል ስለቆዬ በሚል መነሻ የፌደራሉ መንግስት የስራቋንቋ እንዲሆን በህገ መንግስቱ ተወስኗል፡፡ ኦሮምኛስ ኦሮምኛ በሀገሪቱ በርካታ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ነው፣ ሆኖም ቋንቋው ከኦሮሚያ ውጪ በሁለተኛ ቋንቋነት እምብዛም አገልግሎት አይሰጥም፣ ልክ እንደ ትግርኛና […]