”ጅል ሲጃጃል እቃ ይፈጃል!” ትል ነበር እትዬ አሰግድ -አቤ ቶኮቻው

እኔ የምለው አቶ ቴውዶሮስ አድሃኖም አለቅጥ አልተጃጃሉባችሁም፤

11053435_899845720060171_4319992472663135525_nባለፈው ጊዜ ሃያ ሚሊዮን ዶላር ተሸለመች ያሏትን ህጻን ልጅ ለምን ዋሽተው እንዳስዋሿት አይገባኝም። እሺ እውነት ነው እንኳ ቢባል… ልጅቷ ለጋራሙለታ ሰዎች ትምህርት ቤት ይገንባ ብላለች… ይሄንን ያክል ብር የሚያወጣ ትምህርት ቤት ከየት አምጠተው ሊገነቡት ነው። እንዴ… አሁን ቁጭ ብለን ስናስበውኮ ብሩ የተዬ………..ዬ ለሌ ነው። ሰውየው ቁጥር አያውቁም ወይስ የጋራ ሙለታ ህዝብ ቁጥር አያውቅም ብለው ነው!

ሌላ ደግሞ ዛሬ በለቀቁት ፎቶግራፍ ልደታቸውን ለማክበር የውስኪ መዓት ደርድረው ፎቶግራፍ ተነስተው ለጥፈውልናል። ውስኪውን ገና ሳይጠጡት እንዴት ሞቅ አደረጋቸው! ያለሞቅታ ከሆነ እንዲህ ያለውን ስህተት የሚሰሩት… እውነትም ”ጅል ሲጃጃል እቃ ይፈጃል” የሚለው ተረት ለርሳቸው ካልሆነ ለማንም አይሆንም። እኛ እንኳ ካቅማችን እኮ ጠጅ ስንጠጣ የተነሳነውን ፎቶ አልበማችን ውስጥ እንጂ ፌስቡካችን ላይ አንለጥፍም… ባጋጣሚ አዳኝ ካሜራ ካገኘን እንኳ… ”ቆርጦ ቀጥል” ቴክኖሎጂ ነው ጉድ ያደረገን ብለን እንቸቃጨቃለን.. ሃሃ ቆይ ግን እርሳቸው… አሁን ምርጫ ምረጡኝ ሲሉ ቀጣይነት ላለው ልማት ነው ቀጣይነት ላለው ውስኪ… ፍረዱኝ እስኪ…. ኪኪኪ…
የምር ግን አቶ ቴውድሮስ አድሃኖም አንዳች የሚያድናቸው ሃይል ይፈልጋሉ! እውነት ታመዋል።

The post ”ጅል ሲጃጃል እቃ ይፈጃል!” ትል ነበር እትዬ አሰግድ -አቤ ቶኮቻው appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.