ዜና አትሰሙ ስብከት ክርስቶሳዊ አይደለም
ክርስትና ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ የሚል አጅግ በሳል የስው ልጆችን ከግፍ የሚያወጣ ግፍና ግፈኞችን የሚፋለም አንጂ በህዝቦች ላይ ግፍ አየተፈጸመ ዝም በሉ ወይንም ግፈኞችን ሺ አመት ያንግስ የሚል የግፍ ተባባሪ አይደለም፥፥በሰይጣንና በአለም ሴራ የክርስቶስ ቀና ትምህርት ተጣሞ ባርያ ፍንገላ ቅኝ አገዛዝ በክርስቲያን ነን ባዮች በታሪክ ቢፈጸምም ክርስትናም ሆነ መሪው ኢየሱስ ክርስቶስ ግፍና መከራን የሚቃወሙ የሚፋለሙ ናቸው፥፥
ሚዲያ በጎ ነገሮችን አንደሚያቀርብ ሁሉ ክፋትንም ያቀርባል፥፥ ታዋቂው ኒውዮርክ ታይምስ አንደተናዘዘው ሚዲያው ለዘመኑ ሞራል ውድቀት ተጠያቂም መንስኤም ነው፥፥ በበጎ መልኩ በሃገራችን ኢትዮጲያ ሳይቀር ሚዲያ ለህዝቦች ቆሞዋል ዛሬም መከራና አስራት ስደት አየደረሰበት ለህዝቦች መወገኑን አያሳየ ነው፥፥ሰባኪው ከመሰሎቻቸው ጋር ስርአት በጎደለው ስብከት ምእመናንም ሆነ ሚዲያውን ለዘለፉበት ንስሃና ይቅርታ ይጠበቅባቸዋል፥፥በዚህ አጋጣሚም ህዝቦችን በግፍ አገዛዝ ሲጎዱ ቆይተው አሁን በውጭ ሃገር ሚዲያ የሚቀርቡት ሁሉ አንዲሁ ይፋ ንስሃና ይቅርታ ያድርጉ፤፤
ዲጎኔ ሞረቴው ፓስተር የቀድሞ ብስራተወንጌል፨ የምስራች ድምጽ ባልደረባ ከአሜሪካ
The post ዜና አትሰሙ ስብከት ክርስቶሳዊ አይደለም appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.