የዛሬ የቂሊንጦ አጭር ቆይታ
ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ
አብርሃ ደስታን መጠየቅ ከጀርባ ሰው ያስከትላል
‹‹ዕድሜያችንን መቼ ሰራንበት፣ ልደት ማክበርም ያስፈራኛል፡፡ እንኳን ተወለድክ ላላችሁኝ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ››
ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ
ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ከወዳጄ አቤል አለማየሁ ጋር ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት አምርተን ነበር፡፡ አካሄዳችን በዞን ሁለት የሚገኙትን አብርሃ ደስታን፣ ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉንና ጦማሪ አጥናፍ ብርሃንን ለመጠየቅ ነው፡፡