ማዕበል ተነስቶ – ግጥም

በኩባያ ውሃ ማዕበል ተነስቶ

ሁሉን ሲያናውጠው ውሽት ስሩን ሰዶ

እኛም ተሳፋሪ በጊዜአዊው ጀልባ

በዘር ተጠግተን እንጀራ ልንበላ።

አክ እንተፍ በለው አንተ ሰው ይቅርብህ

እልፍ እያለቀሰ አይበጅም መሳቅህ።

ጊዜ – ጊዜ የለው ያልፋል እንደ ጥላ

የመኖር ጉም ይዞህ መስሎህ የማይነጋ

ከበዙዎች ነጥቀህ ፎቆችን በትሰራ

አርቅህ በታኖር ንዋይ በጆኒያ

ጨለማው ሲረታ በብርሃን ሲተካ

የት ልትደበቅ ነው ብርሃኑ ሲመጣ?

(አደፍርስ ተሰማ – 2003 ዓ.ም)