በሆስፒታል ፍቅር የወደቀው ቻይናዊ Chinese Man Refuses to Leave Hospital for 3 Years & Has to Be Forcibly Removed by Police


ብዙዎቻችን ሆስፒታልን ስናስብ ከእርሡ ጋር ተያያዥ ሆኖ የሚታየን የህመምና የሞት ስሜት ምቾት የሚሠጥ አይደለም፡፡ ስለዚህ ለአንድ ቀን እንኳ ሆስፒታል ውስጥ መተኛት እንመኝም፡፡ የሃምሳ አምስት ኣመቱ ቻይናዊ ግን ጤንነቱ ተመልሶለት እንኳን ከሆስፒታል ለመውጣት ፈቃደኛ አልሆነም ነበር፡፡ ቼን የተባለው ይህ ቻይናዊ እ.ኤ.አ ነሐሴ 2011 በአደጋ ምክንያት አነስተኛ ጉዳት ገጥሞት ቤይጂንግ ወደሚኘው አንድ ሆስፒታል ለህክምና ሄዶ ነበር፡፡ ህክምና አግኝቶ ከተመለሠ ከሁለት ወራት በኋላ በድጋሚ ወደ ሆስፒታሉ ተመልሦ የእግር ህመም እንደተሠማው ይገልፅና ይገባል፡፡ የህክምና ባለሙያዎቹ ለሦስት ወራት ቆይቶ እንዲታከም ካደረጉ በኋላ ወደ ቤቱ እንዲመለስ ቢነግሩትም እርሱ ግን አሻፈረን አለ፡፡ ለሦስት ዓመት ያህልም ከሆስፒታል ሳይወጣ ቆየ፡፡
ሆስፒታል እኔን የመንከባከብ ሃላፊነት አለበት የሚለው ቼን ወጪውን መክፈል ባለመቻሉ ከ2012 (እ.ኤ.አ) በኋላ የሚያገኘው የህክምና አገልግሎት ቢቋረጥም ከሆስፒታሉ ሣይወጣ ቆይቷል፡፡ የልጁን ሠርግ እንኳ ለማየት ወደ ቤቱ አልተመለሠም ነበር፡፡
ሰውየው ሙሉ በሙሉ ጤነኛ መሆኑን የሚገልጹት የሆስፒታሉ ኃላፊዎች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውት ከተኛበት አልጋ ላይ በግድ እንዲነሣ አድርገዋል፡፡ በፓሊሶች አማካኝነትም ሆስፒታሉን ለቅቆ ቤይጂንግ ከተማ ውስጥ ወደሚገኘው ቤቱ ገብቷል፡፡ ከሆስፒታል አልጋ ጋር በፍቅር የሚያሰወድቅ አመል እንዴት ያለ ይሆን!

Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።