ከገደብ በላይ ዕጩዎች ሲመዘገቡ – ባለፈው ምርጫና በዕጣ መሠረት ይለያሉ፡- የምርጫ ቦርድ ኃላፊ

(ምህረት ሞገስ) በመጪው ግንቦት 2007 ዓ.ም በሚካሄደው አምስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በአዲስ አበባ ብቻ 25 የፖለቲካ ፓርቲዎች 328 ዕጩ ተወዳዳሪዎችን አስመዝግበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ)፣ መላው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት)፣ የኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) እና ሰማያዊ ፓርቲ ለአዲስ አበባ የምርጫ ክልል ለተዘጋጁ 23 ወንበሮች እያንዳንዳቸው 23 ዕጩዎችን አቅርበዋል፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ሃምሳ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከስድስት ሺ በላይ ዕጩዎችን አስመዝግበዋል፡፡ ይሀ ሁኔታ ካለፉት ምርጫዎች አንጻር ሲታይ እንግዳ ነገር ነው። በተሻሻለው የምርጫ ህግ መሰረት በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ መወዳደር የሚችሉት ዕጩዎች ቁጥር 12 ብቻ ናቸው። በተጨባጭ ግን በአሁኑ ወቅት በአንድ የምርጫ ክልል እስከ 19 የሚደርሱ ዕጩዎች መመዝገባቸውን የምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ይህ እውነታ ከምርጫ ህጉ አንጻር እንዴት ይታያል? መፍትሄውስ ምን ይሆን? የተመዘገቡት ሁሉ በምርጫው ይወዳደራሉ? ወይንስ ሌላ አማራጭ ይኖራል? በማለት በምርጫ ቦርድ የአገልግሎቶችና ግንኙነት ዘርፍ ምክትል ዋና ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላን አነጋግረን ቀጣዩን መረጃ ይዘን ቀርበናል፡፡ አዲስ ዘመን፡- ዘንድሮ በሚካሄደው በአምስተኛው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ምዝገባ ላይ የተለየ ነገር መከሰቱ ተሰምቷል። ጉዳዩን ቢያስረዱኝ? አቶ ወንድሙ፡- በዘንድሮው ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ማስመዝገብ ላይ የተከሰተውና ለየት ያለው ነግር በምርጫ ክልሎች ዘንድ የዕጩዎች ቁጥር መብዛቱ ነው፡፡ በ1999 ተሻሽሎ በወጣው የምርጫ ሕግ […]