እስሩ ቀጥሏል – የአራና አባል እጩ ለፓርላማ ተወዳዳሪ ታሰሩ! – አምዶም ገብረ ስላሴ ከትግራይ እንደዘገበው
ዓረና-መድረክ ወክልለው ለፌደራል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ሁነው የቀረቡት ኣቶ ወልደገብርኤል ሃይሉ ታሰሩ። የኣፅቢ ወንበርታ ዓቃቤ ህግ ያቀረበላቸው ክስ ታስሮው በመኪና ተጭኖው ወደ ፖሊስ ጣብያ ሲወሰዱ ፖሊሶቹን ደብድበሃል፣ ሰድበሃል የሚል ነው።
የክሱ መነሻ በነሃሴ 5 / 12/ 2006 ዓ/ም ማታ 3 ሰዓት ኣከባቢ 9 ፖሊሶችና የወረዳው የፀጥታሃላፊዎች ከቤት ኣስወጥተው እየደበደቡ በመኪና ጭነው ወደ ኣፅቢ ከተማ ሲወስዷቸው ነው።
በወቅቱ ኣቶ ወልደገብርኤልና ኣቶ ሙሉ ኣባይ( በኣፅቢ ወንበርታ የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን) እየፍጢኝ(እጆቹን ወደሗላ በማሰር) እየደበደቡ በመውሰድ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው ይታወቃል። ኣቶ ወልደገብርኤል ሃይሉ እጃቸው የሰበሯቸው ሲሆን በዓይኗቸውና ወገባቸው ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሱባቸው የሃኪም ማስረጃው ያመለክታል።
ኣቶ ሙሉ ኣባይ ደግሞ የፊት ጥርሱ ሙሉ በሙሉ እንዳወለቁት የሃኪም ማስረጃው ያስረዳል። ይህ የተገላቢጦሽ ፍርድ ነው ታድያ ጉዳት የደረሰበት ሰው እንደገና የወረዳው ፍርድ ቤት የ10 ወር ቀላል እስር ቤት እንዲፈረድባቸው ያደረገው ። ጥርሱ የወለቀው ኣቶ ሙሉም የኣንድ ሺ ብር ቅጣት ተፈርዶበታል።
እስቲ ተመልከቱ “..ጅራፍ ራሷ መትታ ራሷ ትጮሃለች..” እንደሚባለው በፖሊስና የፀጥታ ሃላፊዎች ድብደባ ኣካላቸው የጎደለባቸው ዜጎች ተጨማሪ የእስርና የብር ቅጣት ተፈረደባቸው። በወቅቱ እንዲደበደቡና እንዲታሰሩ የተደረገው የዓረና ኣባላት ስለሆኑ ብቻ ነበር።
የትግራይ ህዝብ 60 ሺ ውድ ልጆቹን የከፈለው ይህ መሳይ ፍርድ ሊፈረድበት ነው እምዴ.? ህገ መንግስቱም ማንኛውም ዜጋ በፈለገው ሰለማዊ መንገድ የሚከተል ፓርቲ እንዲደራጅ ይፈቅዳል። ታድያ ህወሓት ምን እየሰራች ነው..?
ይህ ፍርድ የተሰጠው በየካቲት 9ና 10/2007 ዓ/ም በዋለው የወረዳው ችሎት ነው። ለደረሰባቸው ጉዳት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ለመመስረት በሞከሩበት ወቅት “..ለዓረና ኣናስተናግድም..” በሚል ህገመንግስታዊ መብታቸው ተነፍገዋል።
ኣቶ ወልደገብርኤል ሃይሉ ያላቸው ፖለቲካዊ ብቃት በወረዳው ህዝብ ከፍተኛ ተደማጭነት ስላላቸውና በውድድሩ ከተሳተፉ ውጤቱ ለህወሓት የሚመች ኣይሆንም ከሚል ነው።
የምርጫ ህጉን ኣንድ እጩ ተወዳዳሪ እጅከፈንጅ ወንጀል እየሰራ ካልተገኘ ያለ መታሰር መብት ኣለው ይላል።
ህወሓት ህጉ ለራሷ የማይጠቅም ከሆነ ለመሻርና ለመናድ ምንም ኣታወላዳም።
ነፃነታችን በእጃችን ነው..!