ውድቀታቸው የፈጠነባቸው የወያኔ ባለስልጣናት እና ጭፍሮቻቸው ባለሃብቶችን እያስፈራሩ መዝረፍ ጀምሩ::
Minilik Salsawi : ሕዝቡ እየተፈረካከሰ የሚገኘውን ወያኔን በጋራ ታግሎ በማስወገድ ነጻነቱን ማረጋገጥ አለበት::ኢትዮጵያውያን ጨለማን ተገን በማድረግ በታጠቁ በሕወሓት የደህንነት መዋቅር የሚመራ የሽብር ተግባራትን አጥብቆ ስለሚፈራ እና በየጊዜው በሕወሓት ደህንነቶች መሪነት የሚወሰዱ እርምጃዎች በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ስጋትን በመፍጠራቸው በየእስር ቤቱ የሚካሄዱ ሕገወጥ ጸረ ፍትህ ተግባራት እና የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች ሙስና እና ዘረፋ የኢትዮጵያውያን የቀን ተቀን አጀንዳ ሆነው መምጣታቸው ገዢው ፓርቲ ሕዝቡን ምን ያህል እንዳሸበረ ይጠቁማል ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጹ::
የደህንነት ባለስልጣናት እና ጭፍሮቻቸው በከፍተኛ ደረጃ በዘረፋ ላይ መሰማራታቸው ታውቋል:እንደውስጥ አዋቂ ምንጮቹ መረጃ ከሆነ ባለስልጣኖቹ እና ጭፍሮቻቸው የተዘፈቁበት የሙስና ተግባር በተጨማሪ ዘረፋን እና ሴት መድፈርን እንዲሁም የቡድን ወንጀሎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል::በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ባለሃብቶችን በማስፈራራት ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ በማሰር እንዲሁም የሙስና ወንጀል ተገኝቶብሃል ይህን ያህል ገንዘብ አምጣ ካላመጣህ እንገድልሃለን እስከማለት ከመድረሳቸውም በተጨማሪ ይህንን ጉዳይ በየዋህነት ፍትህ ያገኘ መስሎት ለፖሊስ የጠቆመ ባለሃብት በማፈን ንብረቱ በማገድ እና በተለያዩ ስልቶች የተጠየቀውን ገንዘብ እንዲሰጥ በማስገደድ ላይ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል::
በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ባለሃብቶችን በመከታተል እና ደህንነት ቢሮ ድረስ በመውሰድ በሙስና ከታሰረው ስም እየተጠቀሰ … ከሚባል ባለስልጣን እንዲሁም ተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት አለህ ማስረጃ ተገኝቶብሃል በማለት በፈጠራ ወንጀል ባለሃብቱን በመዝረፍ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበረ እና እንዲሁም የአዲስ አበባን ቆነጃጅት ቢሯቸው ድረስ በግብረአበሮቻቸው አፋኝነት እና አስገዳጅነት በመውሰድ ካለፍላጎታቸው አስገድደው በመድፈር ላይ ናቸው ያሉት ምንጮቹ ተራ የደህንነት አባላት ለዚሁ ተልእኮ ተሰማርተው የሚሰሩት ምንም አይነት ወንጀል በቡድን ሲፈጽሙ የሚጠይቃቸው አለመኖሩን የሕዝቡን በደል የከፋ አድርጎታል::ሕዝቡን በማስተባበር እና በመቀስቀስ የተጫነበትን የአምባገነኖች ብትር በጋራ በመታገል አምባገነኖችን እና ጭፍሮቻቸውን ከስልጣን በማስወገድ ነጻነቱን ማረጋገጥ ያለበት ወስኝ ወቅት ላይ መሆኑን ለመናገር እወዳለሁ::#ምንሊክሳልሳዊ