ሰማያዊ ለአንድነት አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ሊያደርግ ነው! – ሰማያዊ ፓርቲ

ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ በአንድነት ፓርቲ ላይ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ፓርቲን ለተቀላቀሉትን የቀድሞ የአንድነት አባላት እሁድ የካቲት 8/2007 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደሚያደርግ ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ፕሮግራሙን ማዘጋጀት ያስፈለገው ምርጫ ቦርድ በአንድነት ላይ በወሰደው እርምጃ ተስፋ ሳይቆርጡ ሰማያዊ ፓርቲን የተቀላቅሉ አባላት ትግሉን ለማጠናከር ያሳዩትን ቆራትነት እና አብሮነት ለማጠናከር እንደሆነ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል፡፡

ከጥር 26/2006 ዓ.ም ጀምሮ ፓርቲውን የተቀላቀሉትና አሁንም መቀላቀሉ የሚፈልጉት የቀድሞው የአንድነት አባላት በፕሮግራሙ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረቡት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሁለቱ ፓርቲዎች አባላት በሰማያዊ ፓርቲ ጥላ ስር አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለ ለውጥ እንደሚያመጡ ተስፋቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡10502165_813527682075480_8666019553634494465_n1456609_1545323512405513_854498771513970591_n

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*