በሽረ ጦርነት ዋዜማ ሻዕቢያ ተስፋ ቆርጦ ነበር – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]
* የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ለሻዕቢያ አሉታዊ የሆነ አቋም ያለማቋረጥ ይይዙና ይወተውቱ ነበር * የህወሓት/ኢህአዴግ ሠራዊት አዲስ አበባ ሲገባ አብሮ የመጣው የሻዕቢያ ተዋጊ ብዛት 300 ገደማ ነበር በሕወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) የትግል ታሪክ እንደ ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ የሚወሰደው የ1981ዱ የሽረ ጦርነት ከመካሄዱ ጥቂት ወራት በፊት ሻዕቢያ በትጥቅ ትግሉ ስኬት ላይ ተስፋ አጥቶ እንደነበር ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ገለጹ፡፡ በሽረ አካባቢ የነበረውን የቀድሞ ሠራዊት 604ኛ ኮር በጋራ የመምታት ሀሳብ ከህወሓት በቀረበ ግዜ፤ ከሻዕቢያ የተሰጠው ምላሽ ‹‹12 ክፍለሀገር ለ2ክፍለሀገር ሞቢላይዝ እያደረገ መቼ ድል እንምናደር አናውቅም – በረጅም ተነል ውስጥ የድል ጭላንጭል አይታየንም›› የሚል እንደነበር አውስተዋል፡፡ ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት ባለፈው ሳምንት ባደረግንላቸው ቃለ-መጠይቅ በሕወሓት እና በተለምዶ ሻዕቢያ ተብሎ በሚጠራው (ያኔ ሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ሕግሓኤ) አሁን ሕዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲ ለፍትሕ) በሚባለው የኤርትራው ገዢ ፓርቲ መሀል ስለነበረው ግንኙነት በሰጡት ምላሽ ላይ ነው፡፡ ከሻዕቢያ ጋር የነበረው ግንኙነት ሚዛኑን የሳተ ነው የሚለውን ክስ የማይጋሩት ጄኔራል ጻድቃን፤ ህወሓት ከአልጀሪያ እስከ ቬትናም፣ ከኩባ እስከ ቻይና ከነበሩ የትጥቅ ትግል ታሪኮች ልምድ ለመውሰድ ይሞክር የነበረ ከመሆኑ አንጻር ከጎረቤቶቹ ከሻዕቢያና ጀብሀ ልምድ መውሰዱ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ስለግንኙነቱ እንደማሳያ ሁለት ክስተቶች እንዲጠቀሱ ተጠይቀው ሲመልሱ፡- በ1973 ገሩ ስርናይ፣ በማርዲ፣ ኡናሽሀቅ፣ ወዘተ በሚባሉት የድንበር አካባቢዎች (ዛሬ አህፈሮም ወረዳ) ለገበሬው መሬት የማከፋፈል ጉዳይ አወዛግቦ የነበረበትን ታሪክ አስታውሰዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቃን በማዕከላዊ ኮሚቴ ተመድበው በአካባቢው ያስተባብሩ የነበረ […]