እንደገና የሞቀው የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ጉዳይ እሰጥ አገባ
ከአምባሣደር ግርማ አስመሮም ጋር ለተደረገው ቃለምልልስ ከታች ያለውን የድምፅ ፋይል ከፍተው ያዳምጡ፡፡
አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ከቪኦኤ የትግርኛ ዝግጅት ክፍል ባልደረባ በትረ ሥልጣን ጋር ያደረጉትን ውይይት ከታች ከተቀመጠው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ባለፈው ሣምንት ለፓርላማቸው ባደረጉት ንግግር የኤርትራ መንግሥት “የአካባቢውን ሰላም በማደፍረስ ቀጥሏል” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሳምንቱ ማብቂያ ጅቡቲን በጎበኙበት ወቅት የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማይል ኦማር ጊሌም በኤርትራ ላይ ተመሣሣይ ክሥ አሰምተዋል፡፡
የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያ ጦሯን “ከተወሰነልኝ ክልል ታስወጣ” እያለ ነው፡፡
በአፍሪካ ኅብረት የኤርትራ ቋሚ ተጠሪ፤ አምባሣደር አርአያ ደስታ ሰሞኑን ለኅብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር ሮበርት ሙጋቤ ደብዳቤ ፅፈው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው የድንበር ጉዳይ በሕግም ሆነ በቴክኒክ ውሣኔ ካገኘና ከተጠናቀቀ ሰባት ዓመታት ማለፋቸውን፤ የኢትዮጵያ ጦር ከኤርትራ ግዛት እንዲወጣና መሬቱ እንዲመለስላቸው ግፊት እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮምም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተመሣሣይ ጥያቄ አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽኑን ውሣኔ መቀበሏን በወቅቱ ማሳወቋን ጠቁመው የመካለሉን ጉዳይ ለመጨረስ ኤርትራ ለውይይት መቀመጥ እንዳለባት ተናግረዋል፡፡
ለዘገባው ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Source:: voanews
The post እንደገና የሞቀው የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ጉዳይ እሰጥ አገባ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.