የአቶ ታደስ ኮስትሬ ቁልቁል የወረደ ውርደት……..በስዊድን የአንድነት የድጋፍ ማህበር
በስዊድን የአንድነት የድጋፍ ማህበር በሓገራችን ኢትዮጵያ ዕለት ተዕለት እየተንሰራፋየመጣውን አምባገነናዊ ስርዓት ያወግዛል፡፡
ሁላችንም እንደሰማነው የወያኔ ኢህአደግ አምባገነን መንግሥት ህዝብ ያቋቋማቸውን የአንድነትትና የሚኢአድን ድርጅቶችፋሸሸታዊ ጡንቻውን በመጠቀም ከዚህ ቀደም በቅንጅት ላይ እንዳደረገው ሁሉ የምረጫ ቦረድ ተብዬው ቡድን አማካኝነትፓረቲዎቹን ለተለጣፊ ስብስቦች አሳልፎ ሰጥቷል ፡፡
ይህንን ሕገወጥ እና አምባገነናዊ ማናለብኝነት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ቆሞ ሊያወግዘውና ሊታገለው ይገባል፡፡
በመሆኑም የአንድነት የድጋፍ ማህበር በስዊድን በሓገራችን የዲሞክራሲ ሥርዓት እሰኪሰፍን የህግ የበላይነት እስኪረጋገጥየሰብዓዊ መብቶች እስኪከበሩ ድረስ ትግሉን እደሚቀጥል ያረጋግጣል ፡፡
ይህ ጥሪ፡–
በዓለም ላይ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያኖች ሁሉ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ እንዲሰፍንና የኢትዮጵያን ሕዝብ እኩልነቱናሰብዓዊ መብቱ ተጠብቆ እንዲኖር ለምትታገሉ የፖልቲካ ድርጅቶች፤ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች እና ግለሰቦች በሙሉ ይህንንአምባገነናዊ ሥርዓት በህበረት እንድንታገልና ሴራውን እንድናከሽፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋልን፡፡
ጥር 23 ቀን 2007 ዓም (ፌብርዋሪ 1 ቀን 2015)
በስዊድን ያአንድነት የድጋፍ ማህበር
ሰቶከሆለም፡፡
The post የአቶ ታደስ ኮስትሬ ቁልቁል የወረደ ውርደት……..በስዊድን የአንድነት የድጋፍ ማህበር appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.