አጣብቂኝ ውስጥ ያለው ኢሕአዴግ ከኦብነግ ለመደራደር ቱርክን ሽምግልና ጠየቀ::

Satenaw Breaking Newsየኢሕአዴግ ባለስልጣናት የቱርክ ፕረዚደንት አቶ ኤርጎዳን የአዲስ አበባን ጉብኝት ወቅት ከኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር(ኦብነግ) ጋር እንደያደራዱራቸው ሽምግልና መጠየቃቸው ታውቋል::በሃይለማርያም ደሳለኝ በኩል የቀረበው ጥያቄ የቱርኩ ፕሬዝዳንት በኦብነግ ላይ ተጽዕኖ አድርገው ከምርጫው በፊት ወደ ሃገርቤት እንዲያስገቡላቸው ተማጽነዋል::

በኤርትራ መንግስት ይረዳል የሚባለው ኦብነግ ድርድሩን ተቀብሎ የሚያስፈልገው ነገር ተሟልቶለት ወደ ድርድሩ እንዲመጣ ከምርጫው በፊት አስፈላጊ የተባሉ የእርቅ ስምምነት ሁሉ እንዲያደርጉ ለፕሬዚዳንቱ ልመናቸውን አቀርበዋል::ጉብኝቱ ጥሩ ሰአት ላይ እንደተደረገ የሚናገሩት የኢሕአዴግ ባለስልጣናት ኦብነግ እስከ ሪፍረንደም ድረስ እድል ሊሰጠው እንደሚችል ኤርትራን ምሳሌ አድርገው ለቱርኩ መሪ አስረድተዋል::

ካሁን ቀደም የኬንያ መንግስት ባለስልጣናት ያደራድሩናል ብለው በእምነት ናይሮቢ የመጡት ሁለት የኦብነግ ስራ አስፈጻሚ አባላት ከናይሮቢ ሂቴላቸው ደጃፍ ላይ በወያኔ ደህንነቶች ታፍነው አዲስ አበባ ማዕከላዊ እስር ቤት ታስረው የሚገኙ ሲሆን የደቡብ እና ምስራቅ እዝ ውስጥ የሚገኙ የወያኔ ሰራዊት አባላት በኦጋዴን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ እንደሚገኝ ከዚህ ቀደም ግንባሩ የለቀቀው ቭዲዮ በገሃድ አሳይቷል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

The post አጣብቂኝ ውስጥ ያለው ኢሕአዴግ ከኦብነግ ለመደራደር ቱርክን ሽምግልና ጠየቀ:: appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.