«የወያኔ ምስጢራዊ መረጃ፤ ጆሮ ያለው ይስማ»
ተክለሚካኤል አበበ
በርእሱ እንዳትሸወዱ
1- ይሄ የኔ ርእስ አይደለም፡፡ የዛሬ 15 ቀን ተክለጊዮርጊስ በተባሉ (የብእር ይሁን የምር ስም አይታወቅም) ሰው የተጻፈን ስም አጥፊ ጽሁፍ የለጠፈው ኢትዮፍሪደም ድረገጽ ወይም የጽሁፉ ደራሲ፤ የአንባቢን ትኩረት ለመሳብ ይመስላል፤ የተጠቀሙበት የመግቢያ ሀይለቃል እንጂ፡፡ ጸሀፊው ለድረገጾች ያላቸውን ቅርበት በመጠቀም፤ እንዲሁም ወያኔ የተባለው ቃል ከተጠራ አንባቢ አያጣራም፤ ወይም ግለሰቡ ላይ ዘሎ ይረባረብበታል በሚልና፤ የስም ማጥፋቱ ሰለባ የሆኑት ሰው፤ ጨዋና እንዲህ ያለው እንከሰላንቲያ ውስጥ ገብተው አይመልሱም በሚል እሳቤ ይመስላል፤ ይሄንን ርእስ ተጠቅመዋል፡፡