እየፈረሰች ያለችውን አዲስ አበባ በመሰንቆ ‘እየገነባት’ ያለው ሀዲስ ዓለማየሁ

ሀዲስ ዓለማየሁ መሰንቆ ተጫዋች ነው። ስለ መሰንቆ አውርቶ አይጠግብም። ዓለም ሙሉ በአንዱ የመሰንቆ ገመድ ቢተሳሰርለት ምኞቱ ነው። ሀዲስ እና መሰንቆን መለያየት አይቻልም ይላል። ስሙንና የሚወደውን መሰንቆ ገምዶ ራሱን ሀዲንቆ ሲል ይጠራል። የመጀመሪያን አልበሙን በቅርቡ ለቋል። አልበሙ እየፈረሱ ባሉት ቀደምት የአዲስ አበባ ሰፈሮች እና ጎዳናዎች ትዝታ የተሞላ ነው።