የመኢአድ ፓርቲ ውዝግብ| ምርጫ ቦርድ ለነአበባው መሐሪ ቡድን የፈረደበት ሙሉ ቃል

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ በተመለከተ መግቢያ በቦርዱ ዕዉቅና ያገኘዉና በስራ ላይ ያለዉ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ የ2001 ዓ.ም ስለመሆኑ፣ ደንቡ የፓርቲዉ አመራሮችም ሆነ አባላት መብትና ግዴታቸዉን አዉቀዉ በእንቅስቀሴዉ ዉስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደሆነ፣ በአመራሩ/በበታች አካሎችና አባሎች መካከል ዴሞክራሲያዊ የሆነ መከባበር ላይ የተመሰረተ አሰራር ለመፍጠር እንደሆነ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ መኢአድ በአሁኑ ጊዜ በሁለት ቡድን በመከፈሉ የፓርቲዉ የስራ እንቅስቃሴ ተገቷል በሚባል ደረጃ ያለ ስለመሆኑ እንረዳለን፡፡ አሁን ተመርጠናል በሚሉት በእነ አቶ ማሙሸት አማረ ቡድን የተፈጸሙ የህግ ጥሰቶችን እንደሚከተለዉ ማንሳት ይቻላል፡፡ 1ኛ. የፓርቲዉ ፕሬዚደንትን ከጠቅላላ ጉባኤ አባላት መካከል መመረጥ እንዳለበት፣ የፓርቲዉ ተ/ምክትል ፕሬዚደንት ደግሞ የጠቅላላ ጉባኤ አባል መካከል ከመሆኑ ባሻገር የማዕከላዊ ምክር ቤት አባል መሆን እንዳለበት የፓርቲዉ ደንብ በአንቀጽ 7.4 እና 4.2.2 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ይሁንና አሁን የተመረጡት ግለሰቦች በ2003 ዓ.ም ከፓርቲዉ አባልነት የተሰረዙ ከመሆኑም በላይ ለሶስት ተከታታይ ወራት የአባልነት መዋጮ ያልከፈለ አባልነቱ ቀሪ እንደሚሆን ስለሚደነግግ ለዚህ ኃላፊነት መስፈርቱን የማያሟሉ ሰዎች በመመረጣቸዉ የህግ ጥሰት ተፈጽሟል፡፡ 2ኛ. ፓርቲዉ አካሂጃለሁ የሚለዉን የጠቅላላ ጉባኤ ዉጤት ሪፖርት፣ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ጥቆማ ሲያደርግ እና ሌሎች የፓርቲዉን ወሳኝ ክንዉኖችን ሲያሳዉቅ በፓርቲዉ ማህተም የተረጋገጠ ሰነድ ማቅረብ እንዳለበት የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 20/1/ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ይሁንና ፓርቲዉ በዚህ አግባብ አረጋግጦ ሊያቀርብ አልቻለም፣ ይባስ ብሎ ህጋዊ ማህተም በሌሎች የፓርቲዉ ቡድን እጅ መኖሩ እየታወቀ ተመሳሳይ […]