Conjoined twins attached at chest and abdomen born in Ethiopia በኢትዮጵያ በደረታቸው የተጣበቁ ሁለት ህጻናት ተወለዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ በደረታቸው አካባቢ የተጣበቁ ሁለት ህጻናት ተወለዱ።

 ነገሩ የሆነው ትናንት ማታ አማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ መረሃ ቤቴ ወረዳ፣ አለም ከተማ፣ እናት ሆስፒታል ውስጥ ነው።  

አንዲት እናት ወደዚህ ሆስፒታል ከ42 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዛ ነው የመጣችው።

 በመጀመሪያው ምርመራ እርግዝናው ችግር አልነበረበትም።  

ነገር ግን በዳግም ምርመራ  በአልትራሳውንድ ስትታይ በሆዷ ውስጥ ሁለት ፅንስ እንዳለ ይታወቃል።  

ፅንሶቹ ደረታቸው አካባቢ የተጣበቁ፣ የጋራ ልብና የየራሳቸው አንገትና ጭንቅላት ያላቸው ነገር ግን ከሆዳቸው በታች ያልተጣበቁ ናቸው።  ፅንሶቹ ለአራት ስዓታት ያህል በህይወት ቆይተው ህይወታቸው ሊያልፍ ቢችልም፥  እናት ግን በሙሉ ጤንነት ላይ ትገኛለች።  

ይህ አይነት ክስተት ከ60 ሺህ ሰዎች ውስጥ በአንዷ ላይ ሊደርስ እንደሚችል ይነገራል።

ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ። Sign up for Email alerts Receive Ethiopian News and Videos by email.