አንዳንዱ ቀን አስገራሚ ነው። – አቤ ቶኮቻው
ጠዋት ላይ የአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ የተወሰደው እርምጃ ምንም እንኳ የሚጠበቅ ቢሆንም በጣም ነው ያበሳጨኝ፤ አንደኛ ፖሊሶቹ እና ደህንነቶቹ ሆነ ብለው ለመደባደብ መሄዳቸውን ሳረጋግጥ አንድ መንግስት እነደ ጥጋበኛ ጎረምሳ ዝም ብሎ በረባውም ባልረባውም ምክንያት ዘሎ ለጸብ የሚጋበዝ ከሆነ እንዴት መንግስት ሊሆን ይችላል… እነደዚ የሰው ልጅን እየቀጠቀጡ በስልታን ላይ መቆየትስ ምን ደስታን ይሰጣል… ስል አብዘቼ ለኛ ሳይሆን ለምንግስቴ ስጨነቅ፤ ድብርት ያዘኝ እና ኮምፒውተሬን ትቼ ወጣሁ።
ትንሽ ቆየሁና አላስችል ብሎኝ በስልኬ ወደ ፌስ ቡክ ጎራ ብል፤ ጃዋር ማህመድ ይሄንን ፎቶ ከኦሮምኛ ገለጻ ጋር አድርጎ ለጥፎት አየሁኝ። ምንም እንኳ ከጃዋር ጋር ሙዳችን አይገጥምም ብዬ ባስብም ይሄንን ገለጻ ሌሎችም በሚረዱት ቋንቋ ቢለጥፈው የተሻለ እንደሆነ አስተያየት ልጻፍለት አልጻፍለት ወይስ ራሱ አስቦ እኪያብራራው ልጠብቅ እያልኩ እያሰብኩ ሳለ ከጥቂት የእንግሊዘኛ ማብራሪያ ጋር ለጥፎት ተመለከትኩ። የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በቅጡ ለመግለጽ ስልኬ አላስቻለኝም ነበር እና ሼር ብቻ አደረኩት!
እንግሊዘኛው በምን ምክንያት እንደተገደሉ ባይገልጽም፤ ከኦሮምኛው ማብራሪያ ላይ ለመረዳት እንደሞከርኩት ከተማ ውበቱ እና ጓደኛው የተገደሉት ”ሽፍታ” ናቸው በሚል ምክንያት ሲሆን ቦታውም ሰላሌ ውስጥ ጎሩ መስቀል ከተማ ነው።
ኢህአዴግ እንደገባች ሰሞን መራቤቴ ውስጥም እንዲህ አይነት ነገር ከአንዴም ሁለት ጊዜ እንደተደረገ ሰምቻለሁ። ሌሎችም ቦታዎች ተደርጎ ሊሆን ይችላል። የአካባቢው መንግስት ይሄንን የማደርገው ለህዝቡ ማሰተማሪያ ነው… ብሎ ሲናገር አፉን ሞልቶ ነበር። (ያኔ ገና ከጫካ እንደወጡ ሰለሆነ የአለም ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን አያወቋቸውም ሊባል ይችላል!)
አሁን በዚህ ዘመን ግን መንግስትን ያክል ነገር ህዝብን ለዛውም ”ለማስተማር” በሚል እንዲህ ያለ ዘግናኝ ስራ ያደርጋል ብሎ ማሰብ በጣም ከባድ ነው። ይሄንን መንግስት እነደ መንግስት መቀበልም እጅግ በጣም ከባድ ነው።
እሺ ሰዎቹ ሽፍታ ናቸው ቢባል እንኳ ይዞ ማሰር ማንን ገደለ። እሺ እጅ አልሰጥ በለው ተታኮሱ እና በተኩስ ልውውጥ ተገደሉ ይባል፤ ሰባዊ ፍጡርን አደባባይ እንዲህ አድርጎ በማስጣት መንግስት ምንደነው የሚያተርፈው። እውን ይሄ ህዝብን ያስተምራል ወይስ ምሬቱን ያብሳል! እነዚህ ሰዎች እኮ አብሮ አደግ አላቸው፤ ዘመድ አላቸው፣ ቤተሰብም አላቸው… ታድያ መንግስት ከስንቱ ተቃቂሞ ይችለዋል…!
ኢህአዴግ መቼ ነው ከጫካ የምትወጣው!!!?????? መቼስ ነው በአለም ህግ የምትገዛው!!!?????
ልብ በሉ ይሄ ከተደረገ ሁለት ወር እንኳ አልሞላውም።






Read more – http://satenaw.com/amharic/?p=4004
The post አንዳንዱ ቀን አስገራሚ ነው። – አቤ ቶኮቻው appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.


