ሰማያዊ ፓርቲን ለመከፋፈል የወያኔ ጎረምሶች ስልጠና እየወሰዱ ነው
በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የሃሰት ምስክርነት የሰጠው ግለሰብ ታወቀ::

ይህ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ወጣት ሄኖክ ተስፋዬ ይባላል፡፡ ሁልጊዜ አርብ በመስጊዶች እየተገኘ ንፁሀን
የእስልምና እምነት ተከታዮችን በሀሰት ውንጀላ የሚያሳስር የወያኔ ጆሮ ጠቢ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችውን ወጣት ወይንሸት ሞላን የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደርሰውን ግፍ ለመከታተል በሄደችበት ወቅት ፀጉሯን ጨምድዶ ከፎቅ ላይ እየጎተተ በማውረድ ከፖሊሶች ጋር በመሆን ከፍተኛ ድብደባ አድርሶባታል፡፡
በወቅቱ በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ለደረሰው ድብደባና ስቃይም ተጠያቂ የሆነ ሰው ነው፡፡ይህ ወጣት በብዙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ በሀሰት ምስክርነት በፍርድ ቤት የሰጠ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም መንግስት ሰማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ እየሰራው ባለው ሴራ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ነን በማለት ፓርቲው እንደተከፋፈለ ለማስመሰል ከባልደረቦቹ ጋር ስልጠና እየወሰደ መሆኑ ታውቋል፡፡
Minilik Salsawi
The post ሰማያዊ ፓርቲን ለመከፋፈል የወያኔ ጎረምሶች ስልጠና እየወሰዱ ነው appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.