አንድነት በዛሬው ዕለት መነሻውን ከደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ መድረሻውን ደግሞ የንጉስ ተክለሀይማኖት ቤተመንግስት ከሚገኝበት ተክለሀይማኖት አደባባይ ያደረገ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዷል፡፡ ፓርቲው ባደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የፓርቲው አባላት፣ ደጋፊዎች እና የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን በሰልፉ ላይ የተገኙት ታዳሚዎችም ምርጫ ቦርድና ገዢው ፓርቲ አንድነትን ለማፍረስ የሸረቡትን ሴራ አውግዟል፡፡


