ዛሬ ከምድረ ኢትዮጵያ የጀግና ድምጽ ሰማሁ። የጣይቱን።

ከዳንኤል ፈይሳ

የወያኔ ቅልብ ፖሊስ ሰልፍ አትወጡም እያለ ድብደባውን አጧጧፈው። እኔም እሪታውን በቀጭኑ ሽቦ ሰማሁት። አብሬ ጮሁ። አብሬ ታመምኩ። ግን አንድ ድምጽ ነበር ከዛ ሁሉ ትርምስ ጩሀት ግርግር መካከል ጮኽ ብሎ የሚሰማ።
“ተላላኪ”
“ባንዳ”
“የባንዳ ተላላኪ” እያለች እየደበደቧት እያቃሳተች ነጻነት የምትል ጀግና። የቻለችውን ሁሉ ለእምየ ኢትዮጵያ የምታደርግ ጀግና። የራሷን ህመም ዉጣ ይዛ ወንድሞቿን በርቱ አይዟችሁ የምትል። ጀግና። የሌሎቹን ማቃሰት አብራ የምታቃስት ጀግና።
ኮራሁብሽ።