ኢሳያስ አፈወርቂ አማርኛ በደንብ አይችልም (ሄኖክ የሺጥላ)

ሄኖክ የሺጥላ

ኤርትራ መሄድ እፈልጋለሁ ። የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ኃይልን መቀላቀል ደሞ አላማዬ ነው ። እስካሁን ለምን እንደቆየሁ አላውቅም ። ስለምፈራ ግን አይደልም ። እኔ የትግሬ ወያኔን መታገል የሚያስፈራ ነገር መስሎኝ አያውቅም ። ለአንድም ቀን ! ይመስክር ያልተነገረው ታሪኬ ! ወይም ከድህረ ገጽ ላይ የተነሳው ታሪኬ ልበል ? ሆድ ይፍጀው !

አሁን ግን ኤርትራ ለኔ የሚሆን / የሚመጥን ክፍት የስራ ቦታ እንዳለ ገባኝ ። የአማርኛ መምህርነት ። አዎ የዔርትራውን መሪ ጋሼ ኢሳያስን አማርኛ ለማስተማር ዔርትራ ብሄድ ደስ ይለኛል ። በአረብኛ ፣ በእንግሊዘኛ ፣ በአፋርኛ ፣ በትግርኛ ቃለ መጠይቅ ሲሰጡ ያየሆዋቸው ፣ የሰማሁዋቸው ፣ ያደመጥኩዋቸው ጋሼ ኢሳያስ አማርኛ የማይናገሩት አባታቸው ” አንድን ቁዋንቁዋ በደንብ ሳትችል አትናገር !” ባሏቸው ምክር እንደሆነ ሰማሁ ። ሌላው ይቅር እንደው ማን ይሙት አሁን ሊሉን የፈለጉት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአማርኛ በተሻለ መልኩ እንግሊዘኛ ይናገራል ለማለት ነው ። መልሱን ለራሳችሁ ! እኔ ግን የወዳጄ ኢሳያስ እስከዛሬ አማርኛ አለመቻል እርር ድብን ነው ያረገኝ። እኔን የኔ ወንድም ያን ሁሉ የጎጃም ነጭ ጤፍ በኮንትሮባንድ ጭነህ ስትዘርፍ የነበረው አንድም አማርኛ ሳትችል ነው ? እንደው ጤፉ እንኩዋ አላስተማረህም ?

ይገርማል አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተማረ ፣ ከብዙ የመሃል ሀገር ሰዎች ጋ አብሮ የተጋለ እና ወዘተ ሰው አማርኛ ስለማልችል ነው በአማርኛ የማወራው ሲል ያሳፍራል ። እኔ ብሆን ይሄን ወሬ ብዬ አላወራውም ነበር !

ለማንኛውም የማይመስል ነገር ስሰማ ህቅ ይለኛል ፣ ያመኛል ። ነገሬ ሁሉ ታሪክ ላይ መሰረት ያደረገ ነውና ይሄ አማርኛ በደንብ ስለማልችል ነው አማርኛ የማልናገረውን እዛው ለሚሰሙህ ። አሁንም እደግመዋለሁ ፣ በዔርትራ በኩል የሚደረገውን ትግል እደግፍ ነበር / እደግፋለሁ / ግን ሾላ በድፍን ሲሆን ዞር በል እላለሁ ። እኔ ትምህርቴን አቁዋርጬ የተሰደድኩበት ሰፈር ነበር ፣ በስም ልጠቅሳቸው የምችላቸው ወዳጆቼ በሸር / በደባ / የተገደሉበት ሰፈር ነው ። ልትከራከር ከፈለክ ጉድህን ነው የማፈላው ! አሁን ለገባንበት ትግል ስለማይጠቅም ትቸው ነው !

አሁንም መሞኘትም ይሁን መጨነቅ ያለብን አይመስለኝም ። የዔርትራ መንግስት ለኢትዮጵያ ህልውና ሲል አንዳችም ነገር አያደርግም ፣ ለረሱ ህልውና ሲል የሚያደርገውን ነገር ግን ለኢትዮጵያ ህልውና ከጠቀመ እቀበለዋለሁ ። እኔ ጉዳዩን የማየው ከዚያ አንጻር ነው ። እንጂ እንደ ልጅ አማርኛ የማይናገረው ለዚህ ነው ፣ ለዚያ ነው ብሎ ማለቱ እንጭጭነት ነው ። እንደኔ እንደኔ እንደ ወሬ መነሳትም ያለበት አይመስለኝም ። ምክንያቱም እኔ እስከማውቀው ድረስ አንድ ሰው ፍቅሩን / ላንተ ያለውን ፍቅር ከሚገልጽባቸው አንዱ ሸራርፎም ቢሆን ያንተ ቁዋንቁዋ በመናገር ነው ። ላንተ ያለውን ክብር የሚያሳይህ እንደዛ ነው ።

ወደ ኢሳያስ ስንመጣ ግን ለኔ ሁኔታውን እንደ አንድ የፖለቲካ ስምምነት ነው የማየው ፣ የሆነ ነገር ይፈልጋል ፣ በራሱ ማድረግ አይችልም ፣ የሆነ ነገር እንፈልጋለን በራሳችን ማድረግ አንችልም ፣ በቃ !