ሰበር ዜና – የአንድነት አባላቶች እስር ቀጥሏል:: በአዲስ አበባ – ደብረማርቆስ – በሸዋሮቢት: በጋሞ ጎፋ ከተማ ቅስቀሳው ተጧጡፏ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በነገው እለት በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያካሄድ ይታወቃል፡፡ በዛሬው እለት ፓርቲው በደብረማርቆስ ከተማ ነገ ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የደብረማርቆስ ህዝብ በቅስቀሳው ወቅት ጥሩ ግብረ-መልስ እየሰጠን ይገኛል፡፡ በነገው እለት ገዢው ፓርቲ አንድነትን ለማፍረስ የሸረበውን ሴራ እንደሚያወግዝ እየገለፀልን ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ፣ በከምባ ወረዳ፣ በሸዋሮቢትና ጂንካ በተመሳሳይ ሰዓት የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዳል፡፡ ስለሆነም ሁላችሁም በያላችሁበት ቦታ በመሆን አጋርነታችሁን እንድታሳዩ ፓርቲው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አንድነት የ23 ወረዳዎች የአዲስ አበባ መዋቅር የበራሪ ወረቀት ቅስቀሳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል ፡፡የአዲስ አበባ ምክር ቤት በፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት የተወሰነውን የማይቀለበስ ውሳኔ በማፅቅ አባላቱ ወደ ተግባር እንዲገቡ ባስተላለፈው መመሪያ በተጠንቀቅ የነበሩት 23ቱ ወረዳዎች በእኩል ሰዓት ቅስቀሳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡የአዲስ አበባ አባላት የተዘጋጀውን በራሪ ወረቀት ምክር ቤቱ ስብሰባ ከመግባቱ በፊት በየወረዳው አሰራጭተው የምክር ቤቱን ውሳኔ በትእግስት ይጠባበቁ እንደነበር እና ውሳኔው እንደተላለፈ ወደ ተግባር መግባታቸውን ለማወቅ ለችሏል፡፡ከማዕከል ይጀመራል ብለው የሚጠብቁ የደህነነት አካላት የሚይዙ የሚጨብጡትን አጥተዋል፡፡የአንድነት የትግል ስትራቴጂ ከኢህአዴግ የደህንነት መዋቅር በላይ መሆኑንም አመላክቷል፡፡
udja9
udja3 - Copy
udja1

udj demp - Copy

udja14 udja7 - Copy udja5 - Copy udja7 udja5 udja2
udja12
udja3

udja13

gamu gamu4 gamu3

The post ሰበር ዜና – የአንድነት አባላቶች እስር ቀጥሏል:: በአዲስ አበባ – ደብረማርቆስ – በሸዋሮቢት: በጋሞ ጎፋ ከተማ ቅስቀሳው ተጧጡፏ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.