ይህ በፎቶው ላይ የሚታየው ወጣት ክብሮም ይባላል፡፡ የህወሓት ሰላይ ነው::9ኙ ፓርቲዎች የ24 ሰዓት ሰልፍ በጠሩበት ወቅት በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችን ያለ ርህራሄ ደብድቧል

gftrይህ በፎቶው ላይ የሚታየው ወጣት ክብሮም ይባላል፡፡ የህወሓት ሰላይ ነው፡፡ 9ኙ ፓርቲዎች የ24 ሰዓት ሰልፍ በጠሩበት ወቅት በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችን ያለ ርህራሄ ደብድቧል፡፡ በተለይ በጣይቱ ልጆች ላይ በጭካኔ ደብደባ ፈጽሞባቸዋል፡፡ ዋናው ስራውም የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን መከታተል፣ ማዋከብ፣ መደብደብና ማሳሰር ነው፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ኢቲቪ አንድነትና መኢአድ ልዩነታቸውን ፈትተው ወደ ምርጫው እንዲገቡ፣ እንዲሁም ሰማያዊ ይቅርታ እንዲጠይቅ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አስተያየት ሰጡ ብሎ ነበር፡፡ እነዚህ የአንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተባት ሰዎች አንድነትና መኢአድ ልዩነታቸውን ፈትተው ምርጫው ላይ በሰላማዊ መንገድ መሳተፍ አለባቸው፣ የምርጫውን ሂደት ማደናቀፍ የለባቸውም፣ ምርጫ ቦርድ የወሰደው እርምጃ ት…ክክል ነው ሲሉ ተስተውለዋል፡፡

ሆኖም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው የተባሉት ‹‹አስተያየት ሰጭዎች›› አብዛኛዎቹ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የመኢአድ አባላትን የሚደበድቡና የሚያሳስሩት የስርዓቱ ደህንነቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል በፎቶው ላይ የሚታየው ክብሮም አንዱ ነው፡፡
ኢቲቪ በተቃዋሚዎች ላይ ሀሰተኛ ክስ መስርቶ ‹‹አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናገሩ›› የሚለው አሊያም ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ እንዲንቆለጳጰሱ የሚያደርገው በእነዚህ ደህንነቶች በኩል መሆኑ ተደርሶበታል፡፡

The post ይህ በፎቶው ላይ የሚታየው ወጣት ክብሮም ይባላል፡፡ የህወሓት ሰላይ ነው::9ኙ ፓርቲዎች የ24 ሰዓት ሰልፍ በጠሩበት ወቅት በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችን ያለ ርህራሄ ደብድቧል appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.