የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት የነገው የተቃውሞ ሰልፍ እንደማይታጠፍ ውሳኔ አስተላለፈ

UDJ calls protest rally in Addis Ababa for Sunday 25 Jan 2015የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አንድነት በምርጫው ለመወዳደር መወሰኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና ኢህአዴግ እያደረጉት ያለውን ስውር ደባ እንዲያቆሙ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቢቆይም መፍትሄ የሚሰጥ አካል ባለመገኘቱ ምክንያት ‹‹መብታችንን ለማስከበር አንለምንም›› በማለት በነገው እለት ማለትም ጥር 17/2007 ዓ.ም በ5 ከተሞች የጠራውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በመንግስትና በተለያዩ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አካላት ፓርቲው የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ቀን እንዲቀይርና ከመንግስት አካላት ጋር ድርድር እንዳያደርግ ጥረት ቢደረግም የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት በዛሬው እለት ባደረገው ልዩ አስቸኳይ የምክር ቤት ስብሰባ ሰልፉ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች እንደሚደረግና ለዚህም የሚያስፈልገውን ክፍያ ለመክፈል መዘጋጀታቸውን በማረጋገጥ ስብሰባውን ማጠናቀቃቸውንና ከአዲስ አበባ በተጫማሪ ሌሎች ከተሞች እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሲልም መመሪያ የሰጠ ሲሆን በአሁን ሰዓት የአንድነት አዲስ አበባ ምክር ቤት ስለነገው ሰላማዊ ሰልፍ የስራ መመሪያዎችንና የድርጊት መርሀግብሮች ላይ እየተወያየ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡