በትግራይ የብረታ ብረት ማቅለጫና ሌሎች 15 ፋብሪካዎች ሊገነቡ ነው
የብረታ ብረት ማቅለጫን ጨምሮ 15 የማምረቻ ፋብሪካዎችን በተለያዩ አካባቢዎች ለማስገንባት ዝግጅት ማጠናቀቁን የትግራይ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ። ለግንባታው 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ካፒታል መድቧል። የኢትዮጵያ ብረት ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በበኩሉ የተለያዩ ክብደት ያላቸው ብረት ብረት ማቅለጥ የሚችሉ ስድስት ፋብሪካዎችን በ6 ወራት ውስጥ ገንብቶ ለማስረከብ ከክልሉ ጋር መስማማቱን አስታውቋል። በክልሉ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሓላፊ አቶ ጥላሁን ታረቀኝ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳሉት የክልሉን የተፈጥሮ ሃብት ነባራዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ የማምረቻ ፋብሪካዎቹ በዘንድሮ ዓመት ይገነባሉ። ”ፋብሪካዎቹ የግብርናውን ምርት ለማቀነባበር የሚያስችሉና ለኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ መደላድል የሚፈጥሩ ናቸው”ብለዋል። የክልሉ የተፈጥሮ ሃብት መሰረት በማድረግ ትልልቅ አራት የማምረቻ ፋብሪካዎች በአላማጣ፣ መቀሌ፣አድዋና ሁመራ ይገነባሉ ሲሉም ተናግረዋል። ባለፈው በጀት ዓመትም ክልሉ በ223 ሚልዮን ብር ወጪ በማምረቻ ኢንዱስትሪ ፣ፋብሪካዎች የፕሮዳክሽን ስራዎች ሊያሰሩ የሚችሉ ማሽኖች ያቀፉ አምስት የማምረቻ ፋብሪካዎች መገንባት መቻሉንም አስታውሰዋል። ከአምስቱ የማምረቻ ፋብሪካዎች በተገኘ ተጨባጭ ልምድና በተፈጠረ ፍላጎት መነሻነት ከክልሉ በተገኘ የገንዘብ ምንጭ እነዚህ ትልልቅ የማምረቻ ፋብሪካዎችን ለመገንባት ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን አስታውቀዋል። ከግንባታ እስከ አጠቃላይ የቴክኖሎጂ ሽግግር ያሉት ስራዎች በዋናነት በኢትዮጵያ ብረት ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን እንደሚከናውን የገለፁት አቶ ጥላሁን የገንዘብ አቅርቦቱን ታዛ በተባለው የክልሉ የካፒታል ዕቃ የፋይናንስ አክስዮን ማሕበር እንደሚሸፈን ገልጸዋል። የአክስዮን ማሕበሩ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አማኑኤል ገብረ ትንሳኤ በበኩላቸው አገሪቱ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በክልሉ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ […]