ዛሬ ከምሽቱ ዜና በኃላ አንድነት ላይ ሊከፈት የታቀደው ሴራ ከሸፈ፡፡ ምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ጻፍኩለት ያለውን አየለ ስሜን አጥቷል!

የኢህአዴግና የምርጫ ቦርድ ድራማ ተዋናይ እያጣ ነው:: ምርጫ ቦርድ ለአቶ አየለ ስሜ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ደብዳቤ መስጠቱን የምርጫ ቦርድ ምክትል ሀላፊ አቶ አዲሱ ገ/እግዚአብሄር ከዚህ ቀደም መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ ዛሬ በምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ተሰጥቷቸው የነበሩት አቶ አየለ ስሜና አቶ ኢሳይያስ ቱሉ እናት ፓርቲያቸውን ይቅርታ በመጠየቅ ተመልሰዋል፡፡ ከእነ አቶ አየለ ቀደም ብለው የተወሰኑ ወጣቶች ከፓርቲው ውጪ ይሰበስቧቸው የነበሩ ሰዎችን የጥፋት ተልዕኮ በመረዳት መመለሳቸው አይዘነጋም፡፡

ገዢው ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ ጋር ተባብሮ አንድነትን ለማፍረስ እየዶለተ በሚገኝበት ሰዓት ላይ ከአንድነት ፓርቲ ለተወሰነ ጊዜ ርቀው የነበሩት አቶ አየለ ስሜነህ፣ የስርዓቱንና አንድነትን እንወክለዋለን የሚሉት ግለሰቦችን ሴራ አጋልጠዋል፡፡ አቶ አየለ ስሜነህ፣ የሰጡት ቃለ ምልልስ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይለቀቃል፡፡ አቶ አየለ በቃለ ምልልሳቸው ወቅት

‹‹አንድነት አንድ ነው!››

ሲሉ ተደምጠዋል፡፡10632760_10205040746652218_5419562326566640030_n (3)

10632760_10205040746652218_5419562326566640030_n