የአንድነት ተወካይ፣ በራዲዮ ፋና የተዘጋጀውን ስብሰባ ጥለው ወጡ!
ራዲዮ ፋና፣ ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር “አምስተኛ ሀገር አቀፍ አጠቃላይ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለማካሄድ “የባለድርሻ አካላት ሚና” በሚል ርዕስ የተለያዩ ‹‹ባለድርሻ›› አካላት የተጠሩበት ውይይት በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ ላሊበላ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የውይይት መሪው የራድዮ ፋናው አቶ ብሩክ ከበደ የነበሩ ሲሆን ኢሕአዴግ፣ ኢዴፓ፣ መድረክ እና ምርጫ ቦርድ የመነሻ ጽሁፎች አቅርበዋል፡፡
የራድዮ ፋናው አወያይ አቶ ብሩክ ከበደ፤
“ለእያንዳንዱ ፓርቲ ሶስት ደቂቃ ብቻ ነው”
በማለት ለማስተዋወቅ ሲሞክር፣ አንድነትን በመወከል የተገኙት አቶ አስራት ጣሴ
‹‹ሶስት ደቂቃ ብሎ መወሰን አይቻልም፤ የአገር ጉዳይ በመሆኑ ካስፈለገ አድረን መነጋገር ይኖርብናል . . . ዋናው ነገር ግን ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ አይደለም፤ ተዓማኒነትም የለውም፤ ምርጫ ቦርድ እና ራድዮ ፋና በሕጋዊ መንገድ የተመረጠን የአንድነት ፕሬዝዳንት ባለማክበር፤ ከጥቂት ግዜያት ወዲህ በምርጫ ቦርድ እና በራድዮ ፋና አማካይነት በሰፊው አፍራሽ ተልእኮአቸው እየተዋወቀ የሚገኙትን ህገ-ወጥ ‹አመራር ነን› ባዮች መሪ የሆነው አቶ ትእግስቱ አወሉን እየተመለከትኩ ነውና ስብሰባውን ጥዬ ለመውጣት እገደዳለሁ፡፡››
