ወያኔ አንድነትን ለማፍረስ ያቀደው ሴራ በሃብታሙ አያሌው አንደበት ከወህኔ ቤት

Habtamu-Ayalew-Andinet

በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የተከሰተውን ሰርጎ የመግባት ሙከራ እና በገዢው ፓርቲ የተደረገውን የተለጣፊ ፓርቲ ምስረታ እጅግ የምቃወመው ሲሆን የአንድነት አመራሮች በጠቅላላ ጉባዬው የተመረጡ እና በአቶ በላይ ፍቃዱ የሚመራው ካቢኔ እንጂ ጥቂት ግለሰቦች በገዢው ፓርቲ ድጋፍ ተሰባስበው አንድነትን የፈጠሩ ተለጣፊ አይደሉም::እኔ ውስከማውቀው ድረስ የአቶ በላይ ፍቃዱ ካቢኔ ሕጋዊ እና በጠቅላላ ጉባዬ የተመረጠ አመራር ነው::

የአንድነትን አመራሮች የምነግራቹ መልእክት ቢኖር አንድነትን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱት ጋር ምንም አይነት ዝቅ ብላቹ ከነሱ ጋር በሚዲያም ሆነ በምንም ቃለ ምልልስ አታርጉ፡፡ እኔም ሆነ ቤስር ላይ የምንገኝ የአንድነት አባላት የአቶ በላይ አመራሮች የምንቀበል እና በኛ ስም ተለጣፊዎቹ እንዳይነግዱ ለማሳሰብ እወዳለሁ:: አሁን አንድነትን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ የኢህኣዲግ ተላላኪዎች እንደሆኑ እና እኛ ለመታሰራችን ተጠያቂ እንደሆኑ አውቆ የአንድነት አባልም ሆነ ደጋፊ በጥንቃቄ እንዲከታተላቸው ለመናገር እወዳለሁ፡፡ ሃብታሙ አያሌው ከቂሊንጦ ወህኒ ቤት::

The post ወያኔ አንድነትን ለማፍረስ ያቀደው ሴራ በሃብታሙ አያሌው አንደበት ከወህኔ ቤት appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.