ቁስል ተራ
ዛሬ ወደ ቢሮ እየመጣሁ በሬዲዮ ስለ አጭበርባሪ ልመናዎች እየሰማ ነበር፡፡ ራሳቸውን በሽተኛ አስመስለው ስለሚለምኑ ሰዎች፡፡ እጃቸውን አጣምመው፣ ሰውነታቸው አቁስለው፣ ዓይናቸውን የጠፋ አስመስለው፤ ጀርባቸውን አጉብጠው ስለሚለምኑ ሰዎች፡፡ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የሚታየው የጉዳት ምልክት ምንም ዓይነት ጥርጣሬን የማያመጣ ነው፡፡
በሰማነው ነገር ላይ እየተወያየን ስንመጣ መርካቶ ‹ቁስል ተራ› የሚባል ቦታ አለኮ አለኝ አንድ ሰው፤ ‹‹ምን የሚደረግበት›› ብዬ ጠየቅኩ፡፡ ‹‹ቁስል የሚሠራበት›› አለኝ፡፡ ‹‹እዚያ ትሄድና ገንዘብ ከፍለህ የምትፈልገውን ዓይነት ቁስል ይሠሩልሃል›› አለኝ፡፡ አይ መርካቶ! አለ ጸጋዬ ገብረ መድኅን፡፤ እስኪ የበለጠ የምታውቁ አካፍሉን፡፡
