አዲስ አበባ በሌሊት በግራፊቲ ጽህፈት አሸብርቃ አደረች!!!

ቅዳሜ ጥር 9/2007

አዲስ አበባ ዛሬ ሌሊት በትግሉ መፈክሮች አሸብርቃ አደረች! ተቃውሞውን እና ለትግሉ ያለውን ቁርጠኝነት በተለያዩ መንገዶች ሲገልፅ የቆየው ሙስሊሙ ማህበረሰብ አሁንም በተለያዩ መንገዶች ተቃውሞውን እየገለፀ ይገኛል።

የግራፊቲ መፈክሮቹ በቦሌ፣ በጀርመን አደባባይ፣ በመካኒሳ፣ በቺቺኒያ፣ በአየር ጤና፣ በጦር ሀይሎች በሚገኘው መጅሊስ ቢሮ አካባቢ፣ በላንቻና በጎተራ፣ እንዲሁም በሌሎች ሰፈሮች ተፅፈው ያደሩ ሲሆን የአካባቢው ጸጥታ ኃይሎችም በሁኔታው መደናገጣቸውን ማወቅ ተችሏል።

በግራፊቲው ከተፃፉት መፈክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:–

«የጨለማ ፈራጆች!»
«ኮሚቴው የህዝብ ነው!»
«ሂጃብ መለያችን!»
«ትግሉ ይቀጥላል!»
«ፍትህ ለኮሚቴው!»

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

ድምፃችን ይሰማ

10405617_892818010769556_2842983660862689031_n

10646689_892818077436216_6186744603608208525_n

10269442_892818037436220_1317333661324676283_n 10690219_892818110769546_6673158360804277920_n 10923473_892817877436236_5318404933193358047_n 10350425_892817827436241_3370485243672254176_n  1907931_892817854102905_4823454683613208375_n 10896920_892817940769563_8482570449715286493_n 12865_892817917436232_6554685172546904693_n

The post አዲስ አበባ በሌሊት በግራፊቲ ጽህፈት አሸብርቃ አደረች!!! appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.