“ትግሬ የብቻው ነው፡ ሸዋ የብቻው ነው፡ ቢገምድር፡ ጎጃም የብቻው ነው፡ እያላችሁ ጎሣ እየለያችሁ ብትጣሉ ምን ትረባላችሁ”

እተጌ ጣይቱ በ1900 ዓ.ም በእየሩሳለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያ የጻፉት ታሪካዊ ደብዳቤ

እተጌ ጣይቱ ሰኔ ፪፱ ፩፱፻ / ስኔ 29 1900 / ዓ.ም በየእሩሳለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያ የጻፉት ታሪካዊ ደብዳቤ።

Empress-Taitu-Betul

Empress-Taitu-Betul

የተላከ፡ ከእቲጊ፡ ጣይቱ፡ ብርሃን፡ ዘኢትዮጵያ።
ይድረስ፡ ለማህበር፡ ዱር፡ ሥልጣን፡ ወደብረ፡ ገነት፡ ዘኢየሩሳለም። እንዲት፡ ሰነበታችኋል። እኔ፡ እግዚአብሔር፡ ይመስገን፡ ደህና ነኝ።
እናንተ፡ ብትስማሙ፡ እርስ፡ በርሳችሁ፡ ብትፋቀሩ፡ አንድነታችሁን፡ ብታፀኑ፡ ይሻላል፡ እንጅ ትግሬ የብቻ ነው፡ ሸዋ፡ የብቻ፡ ነው፡ ቢገምድር፡ ጎጃም፡ የብቻ፡ ነው፡ እያላችሁ፡ ጎሣ፡ እየለያችሁ፡ ብትጣሉ፡ ምን ትረባላችሁ። እኛስ፡ በእየረሱሊም፡ ነገር፡ ይህነን፡ ያህል፡ መድከማችን፡ ይህን፡ ያህል፡ ብር፡ ባንክ፡ አግብተን፡ የዚያን፡ ወለድና፡ ከቤቱ፡ የሚወጣውን፡ ክራይ፡ መስጠታችን፡ እንዳትቸገሩ፡ የሰው፡ ፊት፡ እንዳታዩ፡ ያነን፡ እየባላችሁቸ፡ እኛም፡ የጊታችን፡ ደም፡ ከፈሰሰብት፡ ላይ፡ ዳዊት፡ እንድትደግሙልን፡ እንድታዝኑልን፡ እናንተም፡ ፩ነታችሁ፡ እንዲጸና፡ ብለን፡ ነው፡ እንጅ፡ ገንዘብ፡ ተርፎ፡ ባገራችን፡ በኢትዮጵያ፡ ለምንሰጠው ሰው፡ አጥተን፡ አይደለም። አሁንም፡ ስለ፡ እግዚአብሔር፡ ብላችሁ፡ እናንተም፡ እርስ፡ በርሳችሁ፡ ተፋቀሩ፡ ለኛም፡ ዳዊት፡ ድገሙልን፡ እዘኑልኝ፡ ስትቸገሩ፡ እንዲት፡ የድፍን፡ አውሮፓ፡ መሳቂያ፡ ትሆናላችሁ። አሁንም፡ ይኸው፡ እማሆይ፡ ወለተ፡ መቃብሬ፡ ከዚያው፡ ይሁን፡ ብላ፡ መጥታለችና። አደራችሁን፡ በምኑም፡ በምኑም፡ ነገር፡ እንዳታስቀይሟት፡ እንግዲህ፡ ሷ፡ እንዲህ፡ አድርጉልኝ፡ ብላ፡ የላከችብኝ፡ እንደሆነ እናንተንም፡ እጠላችኋለሁ። እኔንም፡ እንዳስቀይሙኝ። [ሰ]ኔ ፳፱ ቀን፡ ፩፱፻ ዓመት፡ አዲስ፡ አበባ፡ ከተማ፡ ተጻፈ።

tayitu-to-ethiopians-in-jerusalem_1900.ec_

Source- http://welkait.com

The post “ትግሬ የብቻው ነው፡ ሸዋ የብቻው ነው፡ ቢገምድር፡ ጎጃም የብቻው ነው፡ እያላችሁ ጎሣ እየለያችሁ ብትጣሉ ምን ትረባላችሁ” appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.