በአንድነት አባላት እንዴት inspired እነደሆንኩ! – ሶሊያና ሽመለስ (የዞን 9 ቦልገር)
ትላንትና ያየሁት የአንድነት ፓርቲ አባላት ፎቶ ጭንቅላቴ ውስጥ ተቀርጾ ዋለ፡፡ ፎቶው ላይ ምርጫ ቦርድ የጠራው አስገዳጅ ጉባኤ ላይ ለመገኘት መጥተው ፓርቲው ቢሮ ውስጥ መሬት የተኙ አባላት ፎቶነበር፡፡
አንዱን እዛ መሬት ላይ የተኛ አባል አሰብኩት፡፡
“Most probably” ብዙም የኢንተርኔት ተጠቃሚ አይደለም፡፡ ( ኦፍ ላየን ያለው ነገር ደሞ ኦን ላየን ካለው ይበልጥ ተስፋ ያስቆርጣል) አገር ቤትም ሁሉም ሰው ጸጥ ባለበት ዘመን፣ የተቃዋሚ ፓርቲአባል ለመሆን በመድፈሩ፣ በማህበራዊ ኑሮው በሰፈሩ ብዙ እየከፈለ ነው ፡፡ በጉዞ ደክሞት መሬት ላይ ነው የተኛው። እናም በዚያ ትግል ውስጥ ፓርቲውን ለማዳን ተስፋ አድርጓል፡፡ በማግስቱ ስብሰባውንሲካፈል የምርጫ ቦርድ ተወካይ ተለጣፌው የ20 ሰው ስብስብ የጠራውን ስብሰባ ለመካፈል በመሄዱ እንደማይመጣ ይሰማል፡፡ ይሄ በራሱ ተስፋ አስቆርጦ ብርር የሚያደርግ ንዴት ይፈጥራል፡፡ ነገር ግንአማራጭ የለም ይሞክራል፡፡ እሁድ ጠዋት አንደማንኛውም ሰው ለልጆቹ ጋር ያለነጻነት፣ ግን በሰላም ማሳለፍ ይችል ነበር፡፡ የሚብሰው ሰሞ የሚከፍለው መስዋእትነት ምናልባት ውጤት የለሽ ሊመስልምይችላል፡፡ ፓርቲውን ሊያግዱበት ካልሆነም የቀረውን 4 ወር የህጋዊነት ጨዋታ ሲያጫውቱ ከርመው ባለቀ ሰአት ካሻቸው በሉ ተሳተፉ ብለው ሂደቱንም ውጤቱንም ሊቀሙት( ድሮ ውጤት ብቻ ነበርየሚቀሙት) እና ለራሳቸው ጥቅም ሊያውሉት ወይም ደሞ ጭራሽ ሊያባርሩት ይችላሉ፡፡ ግን ማቆም ምርጫ አይደለም፡፡
በአንድነት አባላት እንዴት inspired እነደሆንኩ!
ዝም ብሎ የሚገርመኝ ነገር እንደው እንደኛ በሽብር የተከሰሰ የተሰደደ ሰው ሳይቀር አነዚህ ሰዎች ትንሽ ቦታ ሊከፍቱ ይችላሉ ብሎ ተስፋ አድርጎ ይጠብቃል፡፡ እነሱ ጭራሽ ብቻቸውን ለመሮጥ (ለማሸነፍ አላልኩም- እሱ ታወቀ ነው) ነው ያቀዱት ፡፡ ህግና ስርአቱ ቀርቶ ይሉኝታና ነውር አንኳን አያውቁም ፡፡
ውጤቱ ቀርቶ ሂደቱ የሚሰጠውን ትርፍራፌ እድል ለመጠቀም አንኳን የማይቻልባት አገር ሆናለች ኢትዮጲያ አሁን፡፡ የዛሬው አይነት ቀን ደሞ ትካዜን ይጨምራል ፡፡ እናም ለዚህ ትካዜ ምክንያትከሆነኝ ኢህአዴግ በላይ ( አምባገንን አይን አውጣ ምኑ ይተከዝለታል? ) ምርጫ ቦርድ ነን ብለው የተቀመጡ ግለሰቦች ላይ ነበር፡። ማታ እንዴት ይተኛሉ ? እንዴት የሰፈር ሰው እና ጎረቤት ፌት ቀናብለው ይሄዳሉ ? አንዴት ዴሞክራሲን የሚያህል ስም እና ስራ እየናዱ ፈገግ ይላሉ እያልኩ ሳስብ ነበር፡፡ አንደግለሰብ እንዴት ቢያስቡ ነው ያን ያህል የማይቆቁራቸው ? ( ስሜት እነዳለው ሰው ሳስባቸውዋልኩ)
ፓርቲዎቹን የጥር 4 deadline ተከትሎ ምን አንደተባሉ አልሰማሁም፡፡ ቀልዱን መገመት እችላለሁ፡፡ በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነን የምናደርገው ብቸኛ ነገር የወረደ ቀልዳቸውን በመረጡት ሚዲያእያስነገሩ እውነት ቢያስመስሉት ውሸት ብቻውን ስለቀረበ እውነት አንደማይሆን ለማሳየት ውሸታቸውን ለታሪክ ማስቀመጥ ነው፡፡
ምንም ነገር ቋሚ አይደለምና ከ30 አመት በኋላ “መርጋ በቃና ዴሞክራሲን ገድሎ እንደማህበረሰብ አንኳን መለማመዱን አንዳንጀምረው ያረዘመብን ሰውየ ነው። አዲሱ የሚባለው ደሞ ለጭቆና ህጋዊስም ሲሰጥ ነው የኖረው አንዲህ ነበር፡፡ ምርጫውን 99 በመቶ ኢህአዴግ አሸነፍኩ ሲል ይሄንን ያህል ሰው ገድሎ ይህንን ያህል ሰው አስሮ ይህንን ደባ ሰርቶ ነው ” ብለን እንናገራለን፡፡ አንረሳምምአንሸወድምም፡፡
የመብት ጥሰት ስትሰሙ፣ የምርጫ ቦርድን የዘቀጠ ጨዋታ ስታዬ ብትነግሩን ሰብስበን በመሰነድ የድርሻችንን እንወጣለን፡፡ በስማችን የሚቀለደውን ቀልድ በመሰብሰብ ተባባሪ እንሁን፡፡ ቢያንስ ለመቀየርባንችል ለወደፌት ለመማሪያነት መስቀመጥ እነዴት ያቅተናል?
( ሰማያዊ ፓርቲ ይቅርታ ጠይቁ ሲባሉ የሰጡት መልስ አንዴት አንጀቴን አንዳራሰው)
