ተስፋ ቢሱ የደቡብ ሱዳን ድርድር DW Amharic January 12, 2015 Tagged with Amharic, amharic news, Ethiopia, ethiopian news in amharic, Ethiopians, News in Amharic ከአዲስ አበባ እስከ ታንዛኒያዋ አሩሻ ከተማ በዘለቀው የደቡብ ሱዳን የአንድ ዓመት የድርድር ሂደት የተኩስ አቁም ለማድረግ እና የሽግግር መንግስት ለመመስረት የተደረጉ ስምምነቶች ተግባራዊ መሆን አልቻሉም። በምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለ ስልጣን- ኢጋድ የሚመራው ድርድር በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንደገና ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።