የአንድነት ፓርቲ አባል የሆነው አቶ መሳይ ትኩ፣ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት ገለፀ፡፡

አንድነት ፓርቲ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ የነበረው አቶ መሳይ ትኩ፣ ከጉባኤው ወጥቶ ወደ መኖሪያ ቤቱ በሚያቀናበት ወቅት፤ ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ በሚገኝ የኮሚኒቲ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በፖሊሶች ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት ገልጿል፡፡
አቶ መሳይ ትኩ፣ ባለፈው ሳምንት ‹‹አንድነትን›› ከገዢው ፓርቲ ጋር በመመሳጠር ለማፍረስ ሲሰሩ የነበሩት ግለሰቦችን ሴራ በማጋለጡ የተነሳ፤ በእነዚሁ ግለሰቦች ጠቋሚነት እና ግብረ-አበርነት በዛሬው እለት በከባድ ሁኔታ እንዲደበደብ ምክንያት ሆኗል፡፡ ከግብረ-አበሮቹ መሃል ዳንኤል ሙላት የተባለው (ቅድስተ ማርያም አካባቢ ነዋሪ የሆነው) ግለሰብ ክትትል ሲያደርግበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡10175944_848493945209356_4076377699493018025_n