አርበኞች ግንባር እና ግንቦት ሰባት ተዋሃዱ። ስማቸውም አርበኞች ግንቦት ሰባት ተባለ! አቤ ቶኮቻው
”ይቺን ነው መሸሽ…” አለች ኢህአዴግ!
እንግዲህ የሰላማዊ ትግል አማራጮች በተዘጉ ቁጥር ሌሎች አማራጭ ትግሎችን የመረጡ ታጋዮች ቁጥራቸው እና ህብረታቸው እየበዛ ይመጣል።
”እኔ ሴት ነኝ ጦርነት አልወድም… ነገር ግን በሀገሬ ጉዳይ ገፍቶ የመጣውን ለመመከት ወደኋላ የምል አይደለሁም” እንዳሉት ጣይቱ፤ ጦርነት የሚወደድ ነገር ባይሆንም አማራጭ ከጠፋ ግን ምንም ማድረግ አይቻልም።
ከዚህ በፊት እንደነገርኳችሁ እና እንዳልነገርኳችሁ፤ በ ሁለት ሺህ አመተ ምህረት አካባቢ ጎንደር፤ እነ አርማጭሆ እና እነ አለፋ ጣቁሳ አካባቢ ዞር ዞር የምልበት ጉዳይ ገጥሞኝ ሄጄ ነበር። በዛ አካባቢ ስለ አርበኞች ግንባር የአካባቢው ገበሬ እና የመንግስት ታጣቂው ሳይቀር የሚናገርውን ብትሰሙ… የት አግኝቼ እጅ በነሳኋቸሁ ያስብላሉ።
የአርበኞችን ትህትና እና ቆራጥነት የአካባቢው ሰው አውርቶ አይጠግብም… ዛሬ ከግንቦት ሰባት ጋር ሲዋሃዱ ደግሞ የበለጠ ሞገስ የበለጠ ተወዳጅ እንደሚሆኑ ተስፋ እናደርጋለን!
እኔ በበኩሌ የትግል አይነት ምረጥ ተብዬ ግዴታ ቢጣልብኝ፤ ከኢህአዴግ አስማታዊ ባህሪይ አንጻር በያይነቱ ይሁንልኝ ነው የምለው።
እናም ሰላማዊ ታጋዮቹም በርቱ፤ እምቢ ባዮቹም በርቱ፤ ጸለቶኞቹም እንበርታ!!!