የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል-አቀባይ ኢሳት ወይስ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት? [ኤሊያስ ገብሩ-ጋዜጠኛ]
ኤሊያስ ገብሩ-ጋዜጠኛ
ወሳኝ ሀገራዊ መረጃዎችን ከመንግሥት መጠበቅ የለብንም ይሆን?
በእያንዳንዱ ሀገር ያለ ገዥ መንግሥት የየራሱ መረጃ ለህዝቡና ለዓለም-ዓቀፍ ማኅበረሰብ የመስጠት ባህሪ፣ ልምድና ባህል አለው፡፡ ወሳኝ የሆኑ ሀገራዊ፣ መንግሥታዊና ኅብረተሰባዊ መረጃዎች በሚመለከታቸው የመንግሥታት የመረጃ ሰጪ አካላት በኩል መረጃው ለሚያስፈልገው ሁሉ መድረስ እንደሚያሻ እሙን ነው – በተለይ በዘመነ ግሎባላይዜሽን እና በ21ኛው ክ/ዘመን! ኢትዮጵያን በተለያዩ ጊዜያት ያስተዳደሩ መንግሥታት ‹‹እየመራነው ነው፤ እያስተዳደርነው እንገኛለን›› ለሚሉት ሕዝብ መረጃን የሚሰጡበት የየራሳቸው አካሄድ ነበራቸው፡፡ በአሁን ወቅት ሀገራችንን እያስተዳደረ የሚገኘው ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ነውና በእሱ ላይ ማተኮር ተገቢ ነው፡፡