ዘንድሮ ኢህአዴግን በምንም መልኩ አንፋታውም! አንድነት በድጋሚ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ለእሁድ ጥር ሶስት ጠርቷል።
ኢህአዴግ የእግዴ ልጁ በሆነው ምርጫ ቦርድ በእኩል ከአንድነትና ከመኢአድ ጋር የመረረ ትግል ውስጥ ገብቷል። አንድነት እጅግ በጣም አስደማሚና አስገራሚ የሆነ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄዶ ሁሉም ማሳፈሩ የሚታወቅ ነው። ይህን አይቶ ማመን ያልቻለው ኢህአዴግ ግን እስኪ እስኪ ድገመት ልየው እያለ ነው! ከዚህም በተጨማሪ አንድነትን ከምርጫ ውጪ ለማድረግ ጭፍሮቹን ይዞ ደፋ ቀና እያለ ነው፤ አንድነቶች ግን እጅ መስጠት የታለ እያሉ ፓርቲው ከዘንድሮ ምርጫ ውጭ ለማድረግ የተሸረበውን ሴራ ለማምከን፤ በታሪክም አንድነት ያለምንም ምክንያት ከምርጫው እንደታገደ ለማሳየት አሁንም በድጋሚ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ለእሁድ ጥር ሶስት ጠርቷል። ከዚያ በኋላ አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ዓይኑን በጨው አጥቦ አንድነትን ይዘጋው እንደሆን እናየዋለን። ዘንድሮ ኢህአዴግ በምንም መልኩ አንፋታውም!!