ከ27 -7 ብቻ – አርአያ ተስፋማሪያም
ከ27 – 7 ብቻ
የሕወሀት መሪዎች በረሃ እያሉ የተነሱት ፎቶ ነው ። በፎቶው ከሚታዩት 27 አመራሮች 19 ኙ በተለያየ ጊዜ በመለስ ዜናዊ የተባረሩና የተገደሉ ሲሆን 7 ቱ በስልጣን አንዱ መለስ ዜናዊ ደግሞ በሞት ተለይተዋል ። በመለስ ዜናዊ የተቀነባበረ ሴራ እንዲገደሉ ከተደረጉት መካከል ተክሉ ሃዋዝ ሲሆን ለሞት ያበቃው በኤርታራ ጉዳይ ጠንካራ አቋም በመያዙ ነበር ።
የደህንነት ሹሙ ክንፈ ገ / መድህንና ሃየሎም አርአያ በተመሳሳይ በመለስ እንዲወገዱ የተደረጉ ናቸው ። ቀሪዎቹ ደግሞ ፥ አዋዓሎም ወልዱ ፣ በሪሁ በርሄ ( አረጋዊ )፣ አረጋሽ አዳነ ፣ ገብሩ አስራት ፣ ዘርዓይ አስገዶም ፣ ፃድቃን ገ / ትንሳኤ ፣ የማነ ኪዳኔ ( ጃማይካ )፣ ግደይ ዘረዓፂዮን ፣ ቢተው በላይ ፣ ሀዱሽ ፣ አሰፋ ሃጐስ ፣ ስዬ አብርሃ ፣ መስፍን አማረ ( የኢህአፓ መሪዎችን ጨምሮ በሺህ የሚቆጠሩ ታጋዮችን አሰቃይቶ የገደለና የጃንሆይን ወርቅ ዘርፎ በአሜሪካ የሚኖር ) ሰዓረ ገ / ፃዲቅ ፣ ክብሮምና ሰለሞን ተስፋይ ( ጢሞ ) ሲሆኑ በተለይ የሰሎሞን ባለቤት ኰ / ል ኢሌኒ በመለስ ትእዛዝ ለ11 ወራት ለብቻዋ ታስራ ከፍተኛ ግፍ የተፈፀማባት ናት ። መለስ ይህን ሁሉ ሲያባርሩ ፣ ሲገድሉና ሲያሰቃዩ መኖራቸው ያስገርማል ። ደደቢት የገቡት ‘ ነፃነት ፍለጋ ነው ‘ ቢሉም ሁሉም ግን ለመለስ ነፃነትና መብታቸውን አሳልፈው የሰጡ እንደሆኑ አያከራክርም ። ራሳቸውን ነፃ ሳይወጡ ደግሞ የሌላውን ነፃነት ሊያስከብሩ አይችሉም ። ገብሩ አስራት በመፅሐፋቸው በጥሩ ሁኔታ የድርጅቱን አካሄድ ተንትነውታል ።
