ዶ/ር መረራ ጉዲና – ለ6 ወር ደሞዝ አልተከፈለኝም፣ ፕሮፌሰርነት እስካሁን ድረስ አልተሠጠኝም

(አለማየሁ አንበሴ) ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ድረ-ገጽ በተሰራጨ መረጃ፣የፖለቲካል ሣይንስ መምህርና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጡረታ እንደተባረሩ ቢነገርም መረጃው እውነት አለመሆኑን ከአንደበታቸው ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ሆኖም ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተፈጠረ ችግር እንዳለ ይናገራሉ – ዶ/ር መረራ፡፡ ችግሩ ምን ይሆን? ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ይሄንንና ሌሎች ከመምህርነት ሙያቸው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ጠይቋቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አዲስ አድማስ:- ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተፈጠረው ችግር መነሻው ምንድን ነው? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- ሁሉንም ሲያልቅ መናገር ይሻላል፡፡ ነገር ግን ለ6 ወር ያስተማርኩበት ደሞዝ አልተከፈለኝም፤ መነሻው ይሄ ነው፡፡ ፓርላማ በቆየሁባቸው ጊዜያትም ደሞዝ አይከፈለኝም ነበር፤ የዩኒቨርስቲው ይበቃሃል ተብዬ፡፡ እዚህም እንግዲህ ለ6 ወር በነፃ እያገለገልኩ ነበር ማለት ነው፡፡ አዲስ አድማስ:- ምክንያቱ ተነግርዎታል ? እርስዎስ አልጠየቁም ? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- የቅርብ አለቆች እየተነጋገሩበት ነው የሚል ምላሽ ነው የተሰጠኝ፡፡ ግን ማስተማሬን አላቆምኩም፤ በነፃ እያገለገልኩ ነው ማለት ነው፡፡ ምናልባት መፍትሄ ካልተገኘ መብቴን ለማስከበር ወደ ፍ/ቤት ላመራ እችላለሁ፡፡ አዲስ አድማስ:- በዩኒቨርሲቲው ምን ያህል ጊዜ አስተማሩ? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- እሱ የአደባባይ ሚስጥር ነው፤ ለ28 አመት ፖለቲካል ሣይንስ አስተምሬያለሁ፡፡ አዲስ አድማስ:- በዩኒቨርስቲው በሃላፊነት የመስራት እድል አጋጥሞት ያውቃል? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- አዎ! በሦስት የተለያዩ ጊዜያት የፖለቲካል ሣይንስ ትምህርት ክፍል ተጠሪ ነበርኩ፡፡ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ በትክክል ባላስታውስም ለመጨረሻ ጊዜ በኃላፊነት የሠራሁት ከሦስት ዓመት በፊት ነው፡፡ ኢህአዴግ ከገባ በኋላ ሦስት ጊዜ ሃላፊ ሆኜ ሰርቻለሁ፡፡ አዲስ አድማስ:- የተቃዋሚ ፓርቲ […]