ምርጫ 2007 ውይይት ቁጥር 02 (ግርማ ሞገስ)
የምርጫ 2007 አስርቱ ቃላት
በምርጫ 2007 ቁም ነገር መስራት የሚፈልግ የምርጫ ፓርቲ ከሌሎች እጅግ ብዙ ዝግጅቶች በተጨማሪ ከግንዛቤ ሊያስገባቸው የሚገቡ 10 ነጥቦች ተዘርዝረዋል። ምርጫው ነፃ እና ፍትሃዊ ካልሆነ ከምርጫ መወጣት (ቦይኮት ማድረግ) ጠቃሚ ነው ለሚሉ ወገኖችም መልስ ይሰጣል ይኽ ጽሑፍ። መልካም ንባብ።
አቶ ግርማ ሞገስ
(1) መንግስት በስልጣን መኖር የሚችለው፥ (ሀ) ህጋዊነት የሚለግሰው ህዝብ ሲኖር፣ (ለ) ህዝብ የሙያ ትብብር ሲለግስ፣ (ሐ) ህዝብ የግብር ክፍያ ትብብር ሲያደርግ፣ (መ) የመንግስትን የአገር ተፈጥሮ ሃብት እና አገራዊ ኢኮኖሚ ባለቤትነት ህዝብ እሺ ሲል ብቻ ነው። እነዚህን የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ህዝብ አሳልፎ ለገዢው ቡድን አሳልፎ የሰጠው በፍራቻ ወይንም በፈቃደኛነት ሊሆን ይችላል። ያም ሆነ ይህ የእነዚህ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ባለቤት ህዝብ ነው።፡ ስለዚህ ነው የመንግስት ስልጣን ምንጭ ህዝብ ነው –—[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-