Book Review: የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይ
(ታምራት ኃይሌ) ርዕስ፡- የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይደራሲ፡- ሀማ ቱማተርጓሚ፡- ሕይወት ታደሰአጭር፡- ሥነ ጽሁፋዊ ምልከታገምጋሚ፡- ታምራት ኃይሌ የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይ The case of the Socialist Witchdoctor የ 22 አጫጭር ትረካዎች መድብል ሲሆን ትረካዎቹ በሁለት ክፍል ተለይተው ቀርበዋል፡፡ በክፍል አንድ አድራሻቸውን ፍርድ ቤት ያደረጉና በክስ መዝገቦች፤ በክርክሮች፤ በጥፋተኝነት ና በቅጣት ውሳኔዎች ላይ የተመሰረቱ አስራ አንድ ትረካዎች እናገኛለን፡፡ ትረካዎቹ አንድም አስራአንድም ናቸው፡፡ አንድነታቸውንም አስራአንድነታቸውንም በኋላ እመለስበታለሁ፡፡ በክፍል ሁለት እንደዚሁ አስራ አንድ ትረካዎች እናገኛለን፡፡ እንደመጀመሪያው በአንድ ቦታ የሚከናወኑ አይደሉም፡፡ ስለዚህ እነዚህን አንድም አስራ አንድም ናቸው ማለት ባይቻልም ፍጹም አይመሳሰሉም ደግሞ ማለት አይቻልም፡፡ በግድ አንድ ለማድረግ ሳይሆን፤ እንቅልፍ በሚያሳጣ ጸጉር ስንጠቃም ለመለያየት ሳይሆን በዚህ በሁለተኛው ክፍል ውስጥ ከተዘረዘሩት ትረካዎች መካከል በአንደኛው ማለትም “በሽብር ሚዛን አስር” መግቢያ ላይ የምናገኘው ኃይለ ቃል የቀሩትን ትረካዎች የጋራ ፍሬ ነገር በማስረዳት ረገድ ለጥቅስ የሚበቃ ይመስላል፡፡ እንዲህ ይላል፡፡ ትረካ ኢትዮጵያ ውስጥ ተመራጭ የጊዜ ማሳለፊያ ቢሆንም፤አሁንም ጥቂት ተጠራጣሪዎች ከሰማኒያ በመቶ በላይ መሀይም ባለበት አገር ውስጥ ድሮም ሌላ አማራጭ ሊኖር አይችልም በማለት ይናገራሉ፡፡ ለማንኛውም በዕድሜ የገፉ ሰዎች የተካኑበት ትረካ በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ሁኔታ እንደተለወጠ የማይስማማ የለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ አሰቃቂዎቹና አስገራሚዎቹ ታሪኮች የሚተረኩት በሽማግሌና ባልተማሩ ሰዎች ሳይሆን በተማሩ ወጣት ካድሬዎችና መገናኛ ብዙሀን ተብሎ በሚጠራው አካል ነው፡፡በድሮ ጊዜ በአጠቃላይ ታሪኮች ለዘብ ያሉና ልጆችን ለማስፈራራት ያህል መጠነኛ ምትሀታዊ ጉዳዮች ያሉባቸው ነበሩ፡፡ ስለሚያወሩ ጥንቸሎች፤ስለሸረኛ ጦጣዎች ስለታላላቅ አናብስት፤ስለተንኮለኛ ጅቦች፤ […]