በሽጉጥ አስፈራርቶ ግምታቸው 2ሺህ 450 ብር የሚያወጡ የሞባይል ቀፎዎችን የዘረፈው በ8 ዓመት ከ5 ወር እስራት ተቀጣ Man sentenced to 8 years for robbing two mobile phones worth 2.45 thousand birr at gunpoint
ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ በመጠቀም ግምታቸው 2ሺህ 450 ብር የሚያወጡ ሳምሰንግና ኖኪያ ሞባይሎችን አስፈራርቶ የዘረፈው የ33 ዓመቱ ተከሳሽ ቢኒያም ኃ/ማርያም ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ8 ዓመት ከ5 ወር እስራት እንዲቀጣ ሲል የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ትናንት ታህሳስ 20 ቀን 2007 ዓ.ም ቅጣት ወሰነበት።
ዐቃቤ ሕግ ተከሳሽን በሶስት ክሶች የጠየቀው ሲሆን፤ በ1ኛ ክስ ስር ተከሳሽ ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ ታህሳስ 8 ቀን 2005 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ሲሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15/16 ልዩ ቦታው ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ካለው ኮስሞቲክስ መሸጫ ሱቅ ውስጥ በመግባት እንዳይጮሁ በማስፈራራት፤ ያላችሁን አስቀምጡ በማለት የወግ ቁጥር 394526 የሆነ ሽጉጥ በእጁ ይዞ በመደገንና አንድ ጊዜ ወደመሬትም በመተኮስ የግል ተበዳይ ሂሩት ሃይሉን ግምቱ ሁለት ሺህ ብር የሚያወጣ ሳምሰንግ ሞባይል በመውሰዱ በፈፀመው ከባድ የውንብድና ወንጀል ተከሷል ይላል።
በተመሳሳይ ጊዜና ቦታም ተከሳሽ የሌላኛዋን ተበዳይ ሳምራዊት አስቻለውን ግምቱ 450 ብር የሚያወጣ ኖኪያ ሞባይል ወስዷል ሲል በውንብድና ወንጀሉ ሁለተኛ ክስ ስር ይጠቅሳል። በሌላም በኩል ዐቃቤ ሕግ በሶስተኛ ክሱ ላይ የሚያነሳው ነጥብ ተከሳሹ ይዞት የተገኘው የወግ ቁጥሩ 394526 የሆነ ሽጉጥ ያልፈቃድ በመሆኑ ሕገ-ወጥ ጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ከሶታል።
ከፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ክሶቹን በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች አቅርቦ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት አስረድቷል። ተከሳሽ በበኩሉ ክሶቹን በሚገባ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሎታል።
ይህም በመሆኑ የግራ ቀኙን ክርክር ሲያዳምጥ የቆየው ችሎቱ በትናንትናው ዕለት ተከሳሹን በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
With our e-mail alerts, you will get everything from breaking news about Ethiopia to the days most popular videos, drama, health tips and stories sent straight to your inbox. Sign up for Email alerts
