ምክር እስከመቃብር – (ከኣልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) – በእውቀቱ ሥዩም

የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር እየመጣሁ ነው፡፡ ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው፡፡እናቶች ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን እንዳትጀምሩት ኣደራ፡፡ ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ፡፡የጥይት መከላከያ ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ፡፡ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ እቆጣጠራለሁ፡፡ በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ፡፡ ባሩድ ኣገነፋለሁ፡፡ የታንክ ጎማ እነፋለሁ፡፡በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤ በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …