የአንድነት፣ የሰማያዊና የመኢአድ አባላት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ: – በሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ ዘጋቢ
የአንድነት፣ የሰማያዊና የመኢአድ አባላት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ! ለጥር 19/2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠባቸው!
በሽብር ክስ ተጠርጥረው የመኢአድ፣ የሰማያዊና የአንድነት አመራሮች በዛሬው እለት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡ ሲሆን የአንድነት ፓርቲ ጠበቃ አቶ ገበየሁ እንደገለፁት ከዚህ ቀደም በነበረው ሰነድ፣ አሻራ እና ቃላቸውን ወስደዋል እንዲሁም አስረላጊ ምርመራም አካሂደዋል፡፡ ተጨማሪ ምንም ምርመራ ያደረጉት ነገር ስላልተገኘ ደምበኞቼን የዋስትና መብታቸው ሊጠበቅ ይገባል ብለዋል፡፡ ሆኖም ግን ከጎንደር የተያዙት ከግንቦት ሰባትና አርበኞች ግንባር፣ ከትግራይ የተያዙት ከደሚት ጋር ስልክ ልውውጥ ያደርጋሉ፤ እነዚህን የስልክ ልውውጥ ያደረጉትን እስኪጣራ ድርስ የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ 20 በፈቀደላቸው መሠረት ተጨማሪ 28 ቀን ተቀጥሮባቸዋል፡፡ ከቤተሰብ ጋር መገናኘት አልቻልንም ያሉ ሲኖን ከቤተሰቦቻቸው እና ከጠበቆቻቸው ጋር እንዲገናኙ ሲሉ ችሎቱ አዟል፡፡ ጠበቃቸው እስካሁን ድረስ አቶ እግዳው ዋኘውን ያላገኙት መሆኑን ገና አሁን እዚሁ ችሎት ላይ እንዳገኙትም፤ ሊጠይቁት በሄዱ ጊዜ ስብሰባ ናቸው እና የተለያየ ምክንያት በማቅረብ አንዳላገኙት አክለው ገልፀዋል፡፡ ዛሬ የቀረቡት የአንድነት 4 አባሉ አቶ አለባቸው ማሞ፣ አቶ በላይነህ ሲሳይ፣ አቶ አንጋው ተገኝ፣ አቶ እንግዳው ወኘው ሲሆኑ ከሰማያዊ አቶ አግባው ሰጠኝ እንዲሁም ከመኢአድ 3 አባሉ ለጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም በ 8 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡