Two women referred to ‘terror’ court for driving in Saudi Arabia ሁለት ሳውዲ አረቢያዊያን እንስቶች መኪና በማሽከርከራቸው በሽብር ወንጀል ተከሰሱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁለት ሳውዲ አረቢያዊያን እንስቶች መኪና በማሽከርከራቸው በሽብር ወንጀል ተከሰሱ።

ሎጃን አል ሃትሎል እና ማይሳ አል አሞዲ በሀገሪቱ እንስቶች መኪና እንዳያሽከረክሩ የሚያዘውን ህግ ከመጣሳቸውም ባሻገር በማህበራዊ ድረ ገጾቻቸው ሴቶች መኪና የማሽከርከር መብት ሊኖራቸው ይገባል በማለት ቀስቅሰዋል በሚል ነው ክስ የተመሰረተባቸው።

ይህ አይነቱ ወንጀል ከዚህ ቀደም የሽብር ወንጀልን በሚመለከተው ፍርድ ቤት አልነበረም የሚስተናገደው።

የእንስቶቹ ጠበቃ ድርጊቱ ልዩ በሆነውና የሽብር ድርጊት በሚዳኝበት ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ለማድረግ ማመልከቻ ቢያስገቡም አልተሳካላቸውም።

ክሱ በሀገሪቱ ለረዥም ዘመናት የሚታየውን የሴቶች መብት ረገጣ ለመታገል እንደሚያነሳሳት ነው የ25 አመቷ ሆጃን  የተናገረችው።

ሁለቱ እንስቶች ከአንድ ወር በፊት ነበር በቁጥጥር ስር ውለው እስር ቤት የገቡት። 

ሳውዲ አረቢያ ሴቶች መኪና እንዳያሽከረክሩ በማገድ ብቸኛዋ የአለማችን ሀገር መሆኗን በማስታወስ የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Receive Ethiopian News and Videos by email. Sign up for Email alerts ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።